Your cart is currently empty!
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ለ2018 በጀት ዓመት ለመንገድ ግንባታና ጥገና ስራ የሚያገለግሉ የማሽነሪ እና ትራኮች በቁርጥ ዋጋ መስፈርቶች ከሚያሟሉ አከራዮች ተከራይቶ ማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 17, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የማሽነሪ እና ትራኮች ኪራይ አገልግሎት
የቁርጥ ዋጋ ግዥ ጥሪ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ለ2018 በጀት ዓመት ለመንገድ ግንባታና ጥገና ስራ የሚያገለግሉ የማሽነሪ እና ትራኮች በቁርጥ ዋጋ ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርቶች ከሚያሟሉ አከራዮች ተከራይቶ ማሰራት ይፈልጋል።
| ተ.ቁ | የማሽነሪ እና ትራኮች ዓይነት | ዝቅተኛ የስሪት ዘመን እ.ኤ.አ | ነጠላ ዋጋ+ነዳጅ+ ተ.እ.ታ.በሰዓት | 
| 1 | Dozer (>2300 Hp) | ≥2012 GC | 9,489.00 | 
| 2 | Motor Grader (>140 Hp) | ≥2012 GC | 7,699.00 | 
| 3 | Chain Excavator (Bucket) ≥ 1.6m3 heaped and ≥200Hp) | ≥2012 GC | 7,489.00 
 | 
| 4 | Chain Excavator (Jack Hammer) ≥200 Hp, for jack hammer min. operating weight shall be≥2500 kg and min. impact rate shall be ≥ 350 bpm) | ≥2012 GC | 8,349.00 
 | 
| 5 | Single Drum Roller (>16 ton) | ≥2012 GC | 4,500.00 | 
| 6 | Backhoe Loader (≥1M3 Loader (≥1M3 front Bucket capacity ≥0.5 M3 Backhoe bucket capacity, ≥ 90 Hp) | ≥2008 GC | 3,000.00 
 | 
| 7 | Asphalt Paver (paving width ≥2.5m without screed, Engine capacity ≥150hp, wheeled/chain drive) | ≥2005 GC | 9,527.68 
 | 
| 8 | Water trucks≥13,000Lit | ≥2010 GC | 3,496.00 | 
| 9 | low-bed ≥50 Ton | ≥2010 GC | 5,888.00 | 
1. አከራይ አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ አግባብነት ያለው የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ከአዲስ አበባ ከተማ ኮንስትራክሽን ቢሮ፤ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ ሰርትፍኬት ማቅረብ እና በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድህረ ገፅ (WWW.PPA.gov.et) የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገብ ይኖርባቸዋል።
2. መመዝገብ የሚችሉት አከራይ ድርጅቶች በሰዓት ለኪራይ አገልግሎት ለሚወዳደሩባቸው የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ወይም በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ውልና ማስረጃ የተረጋገጠ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ውክልና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. አከራይ ድርጅቶች እንዳመጣጣቸው ቅደመ ተከተል ፍላጎት እስከሚሟላ ድረስ ተመዝግበው በቅደም ተከተሉ መሰረት ለስራው ይጠራሉ።
4. ለኪራይ የቀረበው የማሽነሪ እና ትራኮች ዓይነት የቴክኒክ ይዘት ከላይ በተጠቀሱት መስፈርች መሰረት ስለመሆኑ የባለስልጣን መ/ቤቱ የመሳሪያ አቅርቦት አስተዳደርና ጥገና ዳይሬክቶሬት እያረጋገጠ ስምሪት የሚሰጥ ይሆናል።
5.የነዳጅ ዋጋ በመንግስት ውሳኔ ሲጨምር ወይም ሲቀንስ ባለስልጣን መ/ቤቱ የዋጋ ማስተካከያ በውሉ ላይ በሚገለጸው ቀመር መሰረት ማስተካከያ ያደርጋል።
6. አከራዮች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ወይም በሬዲዮ ጥሪ ከተላለፈበት ቀን ጀምሮ በስራ ቀን እና ሰዓት በባለስልጣኑ ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 ለምዝገባ የሚስፈልጉትን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ኮፒ ይዘው በመቅረብ መመዝገብ ይኖርባቸዋል።
ባለስልጣን መ/ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ የኪራይ አገልግሎቱን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን (ሳርቤት ፑሽኪን አደባባይ አጠገብ)
ስልክ ቁጥር፡- 011-372-2825
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን