በማ/ኢ/ክ/መንግስት የመስኖ ተቋ/ልማ/አስ/ኤጄንሲ በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት ጥቅል ግዥ ለመግዛት ለኤጄንሲው ባለሙያዎችና ሠራተኞች የደንብ ልብስ ሕጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 17, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ግልጽ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 003/2018

በማ/ኢ/ክ/መንግስት የመስኖ ተቋ/ልማ/አስ/ኤጄንሲ በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት ጥቅል ግዥ ለመግዛት ለኤጄንሲው ባለሙያዎችና ሠራተኞች የደንብ ልብስ ሕጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

በመሆኑም፦

  1. ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የ2018 በጀት ዓመት ዕድሳት የፈፀሙ እንድሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. የግብር ከፋይነት/ቲን እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ፋይናንስ ማስረጃ መቅረብ የሚችሉ፣
  3. የጨረታ አሸነፊ ከሆኑ ከግዣው ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ የሚችሉ፣
  4. ከሚመለከተው የመንግሥት ተቋም ኦንላይን /Online/ ሲስተም የምዝገባ የአቅራብነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የሚሞሉት የአንዱ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል፣
  6. ከ50000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) የሚጨረቱ ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ መያያዝ ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሠረት የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላትና በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋናውን እና አንድ አንድ ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርበቸዋል።
  8. ተጫራቾች ቴከኒካልና ፋይናንሻል ኦርጅናል እና 1 ኮፒ በማዘጋጀት ማቅረብ አለበቸው።
  9. ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ለተወዳደሩባቸው ለደንብ ልብሶች ጫማዎችና ሸሚዞች ለእያንዳንዳቸው ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና ያልቀረባበቸው የዕቃ ዓይነቶች ከውድድር ውጪ ይሆናል።
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሠረተ የባንከ ጋራንቲ ብር 5000.00 /አምስት ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  11. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ከመስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጄንሲ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ይዘው በማቅረብ የማይመለስ 150 ብር ብቻ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ።
  12. ተጫራቾች የዚህን የጨረታ ሰነድ መመሪያ በሚገባ በመረዳት የጨረታ ሰነዳቸውን ሞልተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የመስኖ ተቋማት ልማት አስተዳደር ኤጄንሲ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 9 ቁጥር ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባ አለባቸው።
  13. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል። 15ኛው ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል።
  14. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ እንዲሆኑ እና ለወደፊትም በመንግስት ዕቃ /አገልግሎት ግዥ እንዳይሳተፉ እንደሚደረግ እና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና / እደሚወረስ ማወቅ አለባቸው።
  15. ተጫራቾች ይፋ በሚደረገው ውጤት መሰረት ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች አሸናፊነታቻው ተገልፆ ውል በተፈራረሙ በ15 ቀናት ውስጥ ወለቂጤ በሚገኘው የመስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ መጋዘን ማስረከብ አለባቸው።
  16. ኤጄንሲው በግዥው ዝርዝር ፍላጎት ላይ 20% የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው።
  17. ኤጄሲው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 251 11 365 8470

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት መስኖ ተቋማት ልማትና

አስተዳደር ኤጀንሲ

ወልቂጤ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *