Your cart is currently empty!
በአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የደንበላ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ስፋቱ 57 ካ.ሜ. የሆነ ኮንዶሚኒየም ቤት መሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 18, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የፍርድ ባለመብቶች እነ ወ/ሮ ጽጌ አባይነህ 7 ሰዎች
የፍርድ ባለዕዳ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ኃይሌ መካከል ያለውን የአፈጻጸም ክስ አስመልክቶ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 የካ አባዶ ፕሮጀክት ሳይት 13 የሕንጻ ቁጥር 451፣ የቤት ቁጥር 17 የሆነ በአፈጻጸም ተከሳሽ ፈትለወርቅ ኃይሌ ስም ተመዝግቦ የሚገኘው ስፋቱ 57 ካ.ሜ. የሆነ ኮንዶሚኒየም ቤት በባለሙያ ተገምቶ በቀረበ መነሻ ዋጋ ብር 2,168,394 (ሁለት ሚሊዮን አንድ መቶ ስልሳ ስምንት ሺህ ሦስት መቶ ዘጠና አራት) ግልጽ ጨረታ በማካሄድ በመሸጥ በቤቱ ላይ ያለው የባንክ ዕዳ ለባንክ ከተከፈለ በኋላ የሚቀረውን ገንዘብ ለግራ እና ቀኙ ማካፈል ስለተፈለገ የጨረታ ማስታወቂያ በከለቻ ኦሮሚያ እና አዲስ ዘመን ጋዜጦች ከ10/02/2018 ዓ.ም እስከ 10/03/2018 ዓ.ም. አየር ላይ በሚቆይ የጨረታ ማስታወቂያ በ13/03/2018 ዓ.ም. ከ3፡30 – 6፡30 ጨረታው የሚያካሄዱ ኮሚቴዎች በተገኙበት መሆኑን አውቃችሁ በዚህ ጨረታ ላይ በመሳተፍ ለመግዛት የምትፈልጉ ተጫራቾች የቤቱን ዋጋ ግምት 1/4ኛ ከጨረታው ቀን አስቀድማችሁ በባንክ ሲፒኦ በማስያዝ አዲስ አበባ ከተማ፣ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 በጨረታ የሚሸጠው ቤት በሚገኝበት ኮንዶሚኒየም ግቢ በአካል በመገኘት ተወዳድራችሁ መግዛት የምትችሉ መሆኑን የደንበላ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት አዟል፡፡
ማሳሰቢያ
- በዚህ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ወይም በመወዳደር የቤቱን ዋጋ ግምት 1/4ኛ በሲፒኦ ተይዞ ለጨረታ ኮሚቴ መቅረብ አለበት
- የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ያሸነፈበትን ገንዘብ ጨረታው ከተካሄደበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ መክፈል ይኖርበታል
- ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ፣ በጨረታ የሚሸጠው ቤት የሚገኝበት ኮንዶሚኒየም ግቢ ውስጥ
- የጨረታ ውጤት ለ15/03/2018 ዓ.ም. 3፡30 ላይ ያቀርባል
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 091201352 እና 091918247 ላይ በመደወል መጠየቅ ትችላላችሁ፡፡
በአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የደንበላ ክፍለ
ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት