የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የደንብ ልብስ፣ የዶሮና እንቁላል፣ የታሸጉ ምግቦች፣ የጥራጥሬ እና የስጋ ግብአቶችን ግዢ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 18, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/18

የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት 2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የደንብ ልብስ፣ የዶሮና እንቁላል፤ የታሸጉ ምግቦች፤የጥራጥሬ እና የስጋ ግብአቶችን ግዢ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም የሚወዳደሩ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡

በዚህም መሰረት፡

ለግብር ዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ ክሊራንስ ወይም በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ተፈላጊ ሰነዶች ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀን ሲሆን ሰነድ የሚሸጠው በስራ ሰአት ከሰኞ እስከ አርብ 200 ሰዓት እስከ 1100 ሰዓት የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር/ አዲስ አባባ በሚገኘው ዋናው /ቤት 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 ሽያጭ ክፍል በመክፈል ደረሰኝ ይዘው ቢሮ ቁጥር 208 አቅርቦትና ኮንትራት አስተዳደር ቡድን ቢሮ በመምጣት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ ፡፡ የጨረታ ፖስታውን ፋይናንሻል እና ቅድመ መገምገሚያዎችን /ቴክኒካል ሰነድ/ በተለያየ ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት አሽጎ ማቅረብ አለባቸው፡፡ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የጨረታ ሰነድ ላይ/ የተገለፀውን ብር በሲፒኦ ወይም በባንክ ዋስትና ከቴክኒካል /ህጋዊ ሰነዶች/ ኦርጅናል ሰነድ ጋር ወይም ለብቻው በፖስታ አሽጎ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀን አየር ላይ ይውልና 15ኛው ቀን 800 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 830 ጀምሮ ተጨራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል

ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን እንዳስፈላጊነቱ በከፊል ወይም በሙሉ የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡ አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ስልክ ቁጥር 011 645 4147 / 011 645 3598 / 011 869 4931 ከሳሊህተ ምህረት ማርያም /ክርስትያን ፊት ለፊት የሚገኘው ህንፃ

የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *