Your cart is currently empty!
ሜልባ ፕሪንቲንግ፣ ፐብሊሺንግና ፓኬጂንግ አ.ማ. በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለህትመት አገልግሎት የሚውል ወረቀት ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 19, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ ሜልባ/ብ/ግ/ጨ/004/2018
ሜልባ ፕሪንቲንግ፣ ፐብሊሺንግና ፓኬጂንግ አ.ማ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለህትመት አገልግሎት የሚውል ወረቀት ለመግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የእቃው ዓይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
የጨረታማስያዣ መጠን |
የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
Wood free paper 80 GSM 84CM
|
ቶን |
500 |
የአጠቃላይ ኮንትራት ዋጋ 1% ግን ከ500,000.00 ብር ያልበለጠ |
27/2/2018 ከቀኑ 9፡00 ሰዓት |
27/02/2018 ከቀኑ 9:10 ሰዓት |
በዚህ መሰረት፡
- በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች አግባብነት ያለው የ 2017/2018 የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት፤ በጨረታው መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም የአቅራቢዎች ምዝገባ (suppliers list) ላይ መመዝገባቸውን የሚገልጽ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00/ ሶስት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን ዋና ደረሰኝ ይዞ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከድርጅቱ መ/ቤት የግዥ ዳይሬክቶሬት 2ኛ ፎቅ መውሰድ ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
- ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዋናውንና ቅጅ በተለያየ ፖስታ በማሸግና ሁሉንም በአንድ ላይ በሚይዝ በሰም በታሸገ ፖስታ ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መዝጊያ ተብሎ እስከ ተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ድረስ በአክሲዮን ማህበሩ ዋና መ/ቤት 2ኛ ህንጻ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ይከፈታል።
- አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ : ቦሌ ሚካኤል ኢጃ ዴቬሎፐር ህንጻ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ አጠገብ
ለተጨማሪ ማብራሪያ ስ.ቁ +251 0118550083 – / +251911968780 ፊንፊኔ/ኢትዮጵያ
ሜልባ ፕሪንቲንግ፣ ፐብሊሺንግና ፓኬጂንግ አ.ማ.