Your cart is currently empty!
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተከርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን የተለያዩ ኤሌክተሮኒክስ ቁሳቁሶችን በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢ ደርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Reporter(Oct 19, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
በድጋሚ የወጣ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስ
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተከርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ከዚህ በታች በተቀመጠው ሰንጠረዥ የተመለከቱ የተለያዩ ኤሌክተሮኒክስ ቁሳቁሶችን በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢ ደርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የሚፈለጉት ኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶችን አይነትና ብዛት
| ተ.ቁ | የእቃው አይነት | መለኪያ | ብዛት | 
| 1 | ተንቀሳቃሽ ስልክ (Galaxy Samsung A16,128GB, 8 RAM, 5th Generation | ቁጥር | 8 | 
| 2 | ኮምፒዩተር (HP laptop Computer Core 15, 14/15.6 inch, 8 GB RAM, SSD512, 12th Generation | ቁጥር | 7 | 
| 3 | ኮምፒዩተር (HP laptop Computer Core i7, 14 inch, 1TB SSD, 16 GB RAM,13th Generation | ቁጥር | 1 | 
| 4 | ዲስክቶፕ ኮምፒዩተር(Del Desktop computer Core i5, 12th Generation, 8 GB RAM, 512 SSD, 20 inch) | ቁጥር | 1 | 
| 5 | ፕሪንተር (Hp printer With scanner, HP ቁጥር Leaser MFP 135W) | ቁጥር | 2 | 
ስለሆነም የተዘረዘሩትን የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶችን አይነትና ብዛት ማቅረብ የምትችሉ እንዲሁም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
1. ከዚህ በፊት የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች አቅርቦት ላይ ሰርተው የሚያውቁ ለዚህም ካቀረቡላቸው ድርጅቶች የጽሁፍ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
2. የ2017 ዓ.ም በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው
3. የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ወይም ቲን ተመዝጋቢ የሆኑ
4. ለሚሸጡት እቃ ዋስትና መስጠት የሚችሉ
5. ከገቢዎች የ2018 ዓ.ም ለጨረታ ብቁ መሆናቸው የመገልፅ ማስራጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
6. ከላይ በተራቁ ከ1-5 የተዘረዘሩት መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 7 ቀናት የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ ህጋዊ በሆነ የድርጅታቸው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ (ፕሮፎርማ) በማስፈር በድርጅታቸው ማህተምና ፊርማ አረጋግጠው በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ አዲስ አባባ በሚገኘው የኮሚሽናችን መ/ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አስባቸው፡፡
7. ጨረታው በሰባተኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 7ኛ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥስው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
8. ኮሚሽኑ በተጫራቾች የቀረበውን ጨረታ ሰነድ ላይ የሰፈሩትን የቴክኒክና የፋይናንስ ዝርዝሮችን ከገመገመ በኋላ የጨረታው አሸናፊ የሆነውን ድርጅት ያሳውቃል፡፡
9. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ከኮሚሽኑ ጋር በሚያደረገው የውል ስምምነት መሠረት ጨረታውን ማሸነፉ በተነገረው በ5 ቀናት ውስጥ የኤሌክትሮኒስ ቁሳቁሶችን ትክክለኛነት እና በአግባቡ መሰራታቸውን በኮሚሽናችን ኮምፒተር ባለሞያዎች ፍተሻ ከተደረገ በኋላ እና ኦርጅናልነቱን የሚያረጋግጥ ሠነድ ከታየ በኃላ ቁሳቁሶችን የኮሚሽኑ ዋና መ/ቤት ድረስ አጓጉዞ ማስረከብ ይጠበቅበታል፡፡
10. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ቁሳቁሶቹን አቅርቦ ለኮሚሽኑ እንዳስረከበ በ 5 ቀናት ውስጥ ክፍያ ይፈጸምለታል፡፡
11. ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
አድራሻ፡ አራት ኪሎ ቱሪስት ሆቴል ፊት ለፊት
በኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ጽ/ቤት
ለተጨማሪ ማብራሪያ ስ.ቁ 0911 429 798 / 0943 076 689
አዲስ አበባ