የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ የLED ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ በማወዳደር በዘርፉ ፈቃድ ካለው አቅራቢ ተጫራቾች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 20, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮን/መምሪያ በ2018  በጀት ዓመት ካቀዳቸው ሥራዎች አንዱ የመንገድ መብራት ጥገና በመሆኑ ለዚህ አገልግሎት የሚሆን የLED ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ በማወዳደር በዘርፉ ፈቃድ ካለው አቅራቢ ተጫራቾች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

  1. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፤
  2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፤
  3. ተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፤
  4. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው
    • 4.1. የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለበት
  5. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ (በአዲሱ ከተማ አስተዳደር ሕንፃ) አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር – 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /ለአሥራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ስነድ ብር 700 (ሰባት መቶ ብር) በመክፈል ወስዶ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር ) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲ.ፒ.ኦ (CPO ) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት።
  7. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ (ፋይናንሻል እና ቴክኒካል) በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 (አሥር) ተከታታይ ቀናት በፋይ/ኢኮ/ልማ/መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም ) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8. ጨረታው በ11ኛው ቀን – ከቀኑ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከቀኑ 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል። ይህ ቀን በበዓላት ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል። የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
  9. ተጫራቾች ጨረታ ስያስገቡ ናሙና ይዞ መቅረብ አለበት።
  10. መሥሪያ  ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር 046-212-13-34

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ

ሀዋሳ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *