Your cart is currently empty!
የሞኤንኮ ሠራተኞች ማህበር ለሞኤንኮ ሠራተኞች ክበብ አገልግሎት የሚውሉ የታሸጉ የምግብ ግብአቶች፣ ጥራጥሬዎችና ቅመማቅመሞች፣ አትክልት እና ፍራፍሬዎች ለስድስት (6) ወራት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
2merkato.com(Oct 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የሞኤንኮ ሠራተኞች ማህበር ለሞኤንኮ ሠራተኞች ክበብ አገልግሎት የሚውሉ፣
| ምድብ | የሚቀርበው የእቃ ዓይነት | መግለጫ | 
| 01 | የታሸጉ የምግብ ግብአቶች፣ ጥራጥሬዎችና ቅመማቅመሞች | |
| 02 | አትክልት እና ፍራፍሬዎች | 
ለስድስት (6) ወራት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም እቃዎቹን ተጫርቶ ማቅረብ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታውን ሰነድ ሞኤንኮ ሠራተኛ ማህበር ጽ/ቤት በመቅረብ የእቃው ዝርዝር ያለበትን የጨረታ ሰነድ መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) እየከፈሉ በመውሰድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ከሰኞ- ዓርብ ከጠዋቱ 2፡00 – 10፡00 ሰዓት ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 -6፡00 ሰዓት የጨረታውን ሰነድ ከጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም. እስከ ጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በመውሰድ የጨረታውን ፖስታ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች በአንድ ምድብ እና ከዚያ በላይ መጫረት ይችላሉ፡፡ ጨረታው ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም. ከረፋዱ 3፡50 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ እለት ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሞኤንኮ ሠራተኞት ማህበር ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡ ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የሞኤንኮ ሠራተኞች ማህበር
አድራሻ ፡ ቦሌ ሐያት ሆስፒታል አጠገብ፡፡
ማስታወሻ ፡ ለበለጠ መረጃ ፡ 251+8090-Ex-335