የኦሮሚያ መሬት ቢሮ ቁጥር NCB/04/2018 ለመሥሪያ ቤቱ አገልግሎት የሚውል ጄኔሬተር፣ የተለያዩ የጽሕፈት መሣሪያ፣ የፕሎተሪ ቀለም (plotter ink) እና A-3 መዝገብ ህትመት ከሕጋዊ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 21, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የኦሮሚያ መሬት ቢሮ ቁጥር NCB/04/2018 ለመሥሪያ ቤቱ አገልግሎት የሚውል ጄኔሬተር፣ የተለያዩ የጽሕፈት መሣሪያ፣ የፐሎተሪ ቀለም (plotter ink) እና A-3 መዝገብ ህትመት ከሕጋዊ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

  • ድርጅቶች ዘመኑን ግብር የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና ውል ገብቶ በተባለው ጊዜ ውስጥ ዕቃውን ሙሉ በሙሉ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TN NO/ ያላቸው መሆን አለባቸው።
  • ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር /100/አንድ መቶ/ በመክፈል በኦሮሚያ መሬት ቢሮ 3ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል መግዛት ይችላሉ።
  • ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
  • የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ለመወዳደር ላቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 250,000 (ሁለት በመቶ ሃምሣ ሺህ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች የእቃዎቹን የዋጋ ዝርዝር በጨረታ ማወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ስማቸውን፤ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን በማስፈርና ማህተም በማድረግ የጨረታ ዶክመንቶችን የራሳቸውን የፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒውን ዶክመንቱን በተለያየ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  • ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 2/3/2018 ዓ.ም ከቀኑ በ7፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
  • የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ ወይም ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  • የጨረታው አሸናፊ አካል በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ዕቃወን ጨርሶ ማስረከብ የሚችል።
  • መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ለተጨማሪ መረጃ በዚህ ስልክ ቁጥር መጠቀም ይችላሉ /0949445729/ 0910622700/ 0919519951/ 0946653304
  • አድራሻ፡- ሳርቤት አደባባይን ዞሮ ወደ ቄራ መሄጃ ዋናው አስፓልት 200 ሜትር ላይ የኦሮሚያ ክልላዊ

መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ቅጥር ግቢ ውስጥ የኦሮሚያ መሬት ቢሮ