የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የክሬን ኪራይ አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 21, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡-EEP/TB/FP/NCB/01/2018

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን የአቅርቦት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።

  • ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድረገጽ ላይ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት የካ / ወረዳ 9 ኮተቤ ብረታ ብረት ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና /ቤት፤ የውጭ ዕቃዎች እና አገልግሎት ግዥ ቢሮ የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ተገለጹትን ዕቃዎች በሚመለከት የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/TB/NCB/01/2018 የሚል ምልክት በማድረግ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች ከዚህ በታች በተዘረዘረው የአቅርቦት ግዥ መወዳደር ይችላሉ።

የአቅርቦት ግዥ ዓይነት

የጨረታ ማስከበሪያ

የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት

የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት

የክሬን ኪራይ አገልግሎት ግዥ

ብር 47,500.00 (አርባ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር) ብቻ

ጥቅምት 21 ቀን 2018 . 800 ሰዓት

ጥቅምት 21 ቀን 2018 . 801 ሰዓት

  • ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-558-1725/ 011-558-1916 መደወል ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *