የኦሮሚያ የሕግ ማሰልጠኛ እና ምርምር ኢንስቲትዩት በ2018 በጀት ዓመት አላቂ የፅህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የመስተንግዶ ዕቃዎችን እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 21, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የዕቃ ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ

(Gov-1/2018)

የኦሮሚያ የሕግ ማሰልጠኛ እና ምርምር ኢንስቲትዩት በ2018 በጀት ዓመት አላቂ የፅህፈት መሣሪያዎች የጽዳት ዕቃዎች፣ የመስተንግዶ ዕቃዎችን እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ለመጫረት የሚፈልጉ ሁሉ የዘመኑን የስራ ግብር የከፈሉበትን ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ለመንግሥት መ/ቤቶች እቃ ለማቅረብ የተመዘገቡበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት የአቅራቢነት ዝርዝር ምስክር ወረቀት፣ በጨረታ መሣተፍ የሚያስችል የአገር ውስጥ ገቢ ፈቃድና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት በማያያዝ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ከኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስድስት ኪሎ (አ/አበባ) ከግዥ ንብረት አስተዳደርና ፋይናንስ ክፍል ወይም አዳማ ከተማ አባገዳ አዳራሽ በስተምዕራብ በኩል ከሚገኘው የኢንስቲትዩቱ ዋና ፅ/ቤት 1ኛ ፎቅ ግዥ ንብረትና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት(አዳማ) መውሰድ ይችላሉ።

  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በፖስታ አሽገው እስከ 16ኛ ቀን አራት ሠዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። 16ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን እስከ አራት ሰዓት ድረስ ይሆናል ማለት ነው። ጨረታው በ16ኛው ቀን 4፡00 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የችሎት አዳራሽ ተዘግቶ ወዲያውኑ ይከፈታል።
  • ተጫራቾች የመወዳደሪያ (የጨረታ) ሰነዱን በሚያስገቡበት ጊዜ የጨረታ ማስከበሪያ የኢት.ብር 65,350.60.00 (ስልሳ አምስት ሺ ሶስት መቶ ሃምሳ ከ60/100) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ለጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  • አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈበትን የእቃዎች ድምር ዋጋ 10% /አስር ፐርሰንት/ በባንክ የተረጋገጠ /CPO/ የሥራ ዋስትና በማስያዝ ከኢንስቲትዩቱ ጋር ህጋዊ ውል ይፈራረማል።
  • በአሸናፊ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
  • ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 022-110-0770 ደውሎ ማግኘት ይቻላል።
  • ኢንስቲትዩቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በማንኛውም ጊዜ የመሰረዝ መብት አለው።

ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች መደበኛ የሆነ የሸያጭ ወይም የማሳያ አድራሻ ሊኖራቸው ይገባል።

ዝርዝር መግለጫ ለሌላቸው ዕቃዎች በሙሉ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

የኦሮሚያ የሕግ ማሰልጠኛ እና ምርምር ኢንስቲትዩት