Your cart is currently empty!
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የሰቆጣ ዝናብ አጠር ግብርና ምርምር ማዕከል የቢሮ አላቂ እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የፅህፈት መሳሪያ እቃዎች፣ የደንብ ልብስ እና የመኪና እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 21, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የሰቆጣ ዝናብ አጠር ግብርና ምርምር ማዕከል የቢሮ አላቂ እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የፅህፈት መሳሪያ እቃዎች፣ የደንብ ልብስ እና የመኪና እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይገልጻል።
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፣
3. የግዥው መጠን ብር ከ50,000/ሃምሳ ሺህ ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
4. ተጫራቹ በጨረታው ለመሳተፍ ከላ ከተ.ቁ.1 እስከ 4 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመከፈል ከማዕከሉ ገንዘብ ቤት ቢሮ ቁጥር 14 መውሰድ ይችላሉ።
7. የጨረታ ሰነድ የሚሸጠው ከ10/02/2018 ዓ.ም እስከ 28/02/2018 ዓ.ም ለአስራ አምስት ቀናት ይሆናል።
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር 1% /አንድ ፐርሰንት/ ወይም የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% /አንድ ፐርሰንት/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በሰ.ዝ.ግ.ም.ማ በግዥ ፋይናንስ ን/አሰ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 16 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከ10/02/2018 ዓ.ም እስከ 28/02/2018 ዓ.ም እስከ ጠዋት 4፡00 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፈንብ/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት በቢሮ ቁጥር በ10/05/2016 ዓ.ም በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
11. ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 16 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ፋክስ ቁጥር 033-4-40-04-09 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 033-4-40-11-00 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፡–የሚሞሉት ዋጋ ከነቫቱ መሆን አለበት።
የተጫራቾች መመሪያ፡–
1. ግዥ ፈጻሚው መ/ቤት በአማራ ብሄራዊ መንግስት ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የሰቆጣ ዝናብ አጠር ግብርና ምርምር ማዕከል ስልክ ቁጥር 033-4-40-11-00 ፋክስ ቁጥር 033-4-40-04-09 የቢሮ አላቂ እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ኮምፒውተር፣ የፅዳት እቃዎች፣ የፅህፈት መሳሪያ እቃዎች፣ የደንብ ልብስ የመስክ ዕቃዎች እና የመኪና እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ነው።
2. ተጫራቾች ዕቃዎችን ለማቅረብ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያወጡ የተሰጣቸው ፈቃድ አንድ ዓመት የሞላው ከሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ታከስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግስት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልጾላቸው ቀርበው ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው በአግባቡ ባለመፈጸማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፣ ሆኖም የተወሰደው እርምጃ በማስረጃ የተደገፈ መሆን አለበት።
5. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር / በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ ሰቆጣ ዝናብ አጠር ግብርና ምርምር ማዕከል ግዥና ፋ/ንብ/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 16 ዘወትር በስራ ሰዓት በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።
6. ተጫራቾች በሚያቀርቡት መወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱ ማህተም ያረፈበት መሆን አለበት።
7. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች ጨረታ ያወጣው መስሪያ ቤት ባቀረበው ባለሙያ መሰረት አስፈትሾ ቢሮ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም ላሸነፈባቸው እቃዎች ካስረከበበት ጊዜ ጀምሮ ለአንድ አመት የጥገና ዋስትና መወሰድ ይኖርበታል።
8. በጨረታ ለመሳተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጪዎች ቢኖሩ ማዕከሉ /መስሪያ ቤቱ/ ተጠያቂ አይሆንም።
9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት።
10. ተጫራቾች መጫረቻ ሰነዶቻቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ከ10/02/2018 ዓ.ም እስከ 28/02/2018 ዓ.ም የጨረታ ሰነዱን እስከ ጥዋት 4፡00 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፣ ጨረታው የሚከፈትበት ቀንም በዚያው ቀን በሰ.ዝ.ግ.ም.ማ በግዥ ፋይናንስ ን/አሰ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 16 በ28/02/2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር 1% /አንድ ፐርሰንት/ ወይም የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% /አንድ ፐርሰንት/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
14. አንድ ተጫራች በወጣው የጨረታ ሰነድ ላይ ጥያቄ ወይም ማብራሪያ ቢያስፈልግ ጨረታውን ላወጣው መስሪያ ቤት በጽሁፍ ወይም በፋክስ ቁጥር 033-4-40-04-09 ማቅረበ ይችላል፣ ጨረታውን ያወጣው ማዕከልም ለተጠየቀው ጥያቄ ማብራሪያ የሚሰጥ ሆኖ ሲገኝ ለሁሉም ተጫራቾች በጽሁፍ ወይም በፋክስ መልስ ይሰጣል።
15. የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
16. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
17. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታው ወጪ እንደሚሆን ለወደፊቱም በመንግስት የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፍና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ይወረሳል።
ማሳሰቢያ፡– ዋጋውን ስትሞሉ ከቫት ጋር መሆን አለበት።
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የሰቆጣ ዝናብ አጠር ግብርና ምርምር ማዕከል