Your cart is currently empty!
በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ አዳማ የግብርና ማሸነሪ ማምረቻ ኢንዲስትሪ ለ2018 በጀት ዓመት የአደጋ መከላከያ አልባሳት፣ የመካኒካል ወርከ ሾፕ ዕቃዎች፣ ኮምፒውተሮች፣ የትራክተርና የፓምፕ መለዋወጫ፣ የአየር ኮምፕሬሰር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 21, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨ.ሰ.ቁ፡- NCB-AAMMI-002/2018
በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ አዳማ የግብርና ማሸነሪ ማምረቻ ኢንዲስትሪ ለ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለሰራተኛ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የመገልገያ ዕቃዎችና ለምርት አገልግሎት የሚውሉ የምርት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት-1፡ የአደጋ መከላከያ አልባሳት
- ሎት-2፡ የመካኒካል ወርከ ሾፕ ዕቃዎች
- ሎት-3፡ ኮምፒውተሮች
- ሎት-4፡ የትራክተርና የፓምፕ መለዋወጫ
- ሎት 5፡ የአየር ኮምፕሬሰር
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ያህል ሰነዱን አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በግዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 014 በመገኘት መውሰድ (መግዛት) ይችላሉ።
ተጫራቾች ከሚያቀርቡት እቃ ጋር ተዛማጅ የሆነ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የግብር ክሊራንስ ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የሚያስችል ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
ተወዳዳሪዎች በጨረታው ላቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው።
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተጫራቹ ምርጫ ከሚከተሉት ዓይነቶች አንዱ ሊሆን ይችላል።
(ሀ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፣
(ለ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ የባንክ ጋራንቲው 60 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን አለበት።
ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ (አስር የስራ ቀን) ቀናት በአዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በግዢ ክፍል ቢሮ ቁጥር 014 በመገኘት ሰነዱን በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተገለፀው አስተሻሸግ መሰረት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
ጨረታው የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የሥራ ቀናትን አልፎ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው⁄ በተገኙበት ከታች በተገለፀው አድራሻ በአዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የስብሰባ አዳራሽ ጨረታው ይከፈታል። ቀኑ የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል። የተጫራት አለመኖር ፖስታው ተሟልቶ እስከተገኘ ድረስ ጨረታውን ለመክፈት አያስተጓጉልም።
ኢንዱስትሪው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 022 111 0689/ 09 12 26 46 80 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ፡- አዳማ ከወንጂ ማዞሪያ ተቃራኒ አቅጣጫ 500ሜ ላይ
ስልክ፡- 022 111 0689/ 09 12 26 46 80
ፋክስ፡– 022 111 1866
አዳማ
በኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩፕ አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ