በማዕከላዊ ኢት/ያ ከልል በሀዲያ ዞን የጃጁራ ከተማ አስ/ር ፋ/ጽ/ቤት የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ለኤሌክትሮኒክስ ግዥ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በማዕከላዊ ኢት/ያ ከልል በሀዲያ ዞን የጃጁራ ከተማ አስ/ር ፋ/ጽ/ቤት የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘራዘሩትን መስፋርቶችን የሚያሟሉ አቅራቢዎችን በጨረታ እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

ስለዚህ፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው
  2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው
  3. ግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው
  4. VAT ተመዝጋቢነት ሠርተፍኬት ያለው
  5. የዕቃ አቅራቢነት ሠርተፍኬት ያለው

ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ተከታታይ በ15 ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነድ 200 ብር በጀ/ከ/አስ/ር ገ/ጽ/ቤት በመክፈል መግዛት የሚቻል ሲሆን ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 10,000 በፊደልም /አስር ሺ ብር/ በጥሬ ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ (cpo) የሚጠበቅባቸውን የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋ ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው ፎርማት ብቻ በመሙላት ሰነድ መግዛት የሚቻል ሲሆን ጨረታው እስከ 15ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት የሚያበቃ ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ታሽጎ 5፡30 ላይ የሚከፈት ሲሆን የአንዱን ዕቃ ዓይነት ነጠላ ዋጋ በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስረጃዎቻችሁን በፖስታ በማሸግ ማስገባት የሚቻል ሆኖ በጀጁራ ከተማ አስ/ር ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 09 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት ቀኑ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተባለው ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይሆናል ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ላይገኝ መቅረቱ የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡

ዕቃውን በሀዲያ ዞን በጃጁራ ከ/አስ/ር ፋ/ጽ/ቤት ድረስ የሚያቀርብ ሆኖ የጨረታ ዝርዝር መረጃ የሚሞላበት ፎርማት ኮፒ ከቢሮ ቁጥር 09 ወይም ከግ/ን/አስ/ር ዋና ሥራ ሂደት እንድትወስዱ እናስታውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፦ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኛ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በማዕከላዊ ኢት/ያ ክልል በሀዲያ ዞን የጃጁራ ከተማ አስ/ር ፋ/ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *