Your cart is currently empty!
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት በ2018 ዓ.ም. በጀት ዓመት የID4 እና ID6 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የሰርቪስ ጊዜ ሲደርስ ሙሉ ሰርቪስና ጥገና የሚያደርጉ ጋራዥ ቤቶችን በግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 22, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የግልጽ ጨረታ
ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የID4 እና ID6 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የሰርቪስ ጊዜ ሲደርስ ሙሉ ሰርቪስና ጥገና የሚያደርጉ ጋራዥ ቤቶችን በግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል።
በጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 400 በመክፈል ሰነዱን ከግዢ ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር መግዛት ይቻላል።
1. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ CPO 2% ከአጠቃላይ ዋጋ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
2. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች በዘርፉ ንግድ የተሰማሩበትን በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
4. የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻው በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የአንዱ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር መ/ ቤቱ ቫት እንደተካተተ አድርጎ ይወስዳል።
6. ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ በኮፒውና በኦሪጅናል በየገጹ ማህተም መደረግ አለበት።
7. ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ።
8. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
9. ጨረታው በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ በ4፡00 ሰዓት ተወዳዳሪዎች በአካል ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11. አሸናፊ ድርጅት ውል ከተዋዋለ በኋላ ዋጋ መጨመርና መቀነስ የማይቻል መሆኑ፤
12. መ/ቤቱ ከተገኘው ዋጋ ሳይቀይር እስከ 20% መቀነስ ወይም መጨመር የሚችል መሆኑን።
13. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ስልክ ቁ. 0114-706464
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ካሳንችስ ልማት ባንክ ጀርባ የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎች፤
1. የዘመኑ ግብር የተከፈለበት፣የታደሰ የንግድ ፈቃድና የምዝገባ የምሥክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. በሥራ ዘርፉ ለመሰማራታቸው የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. የቫት ተመዝጋቢ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት