Your cart is currently empty!
በጅማ ዞን በሊሙ ሰቃ ወረዳ መንገድና ሎጀስቲክስ ጽ/ቤት የገጠር መንገድ ላንጦ አለለወርቅ፣ ሞቴ አልጋ ቂልጡ ሙጃ፣ ኮማ-ጨሪ አልጋ፣ ሞቴ-አምባቤላ፣ ኮማ-አሉ ካላላ፣ ጋሌገበታ ሞጆወርጂ፣ ኮማ-ጨራ አሉ ደረባ እና ኮማ-ሳቻኒ መስመር ያለውን መንገድ ወረዳችን ማስጠገን ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በጅማ ዞን በሊሙ ሰቃ ወረዳ መንገድና ሎጀስቲክስ ጽ/ቤት የገጠር መንገድ ላንጦ አለለወርቅ፣ ሞቴ አልጋ ቂልጡ ሙጃ፣ ኮማ–ጨሪ አልጋ፣ ሞቴ–አምባቤላ፣ ኮማ–አሉ ካላላ፣ ጋሌገበታ ሞጆወርጂ፣ ኮማ–ጨራ አሉ ደረባ እና ኮማ–ሳቻኒ መስመር ያለውን መንገድ ወረዳችን ማስጠገን ይፈልጋል
ስለዚህ በዚህ ሥራ ላይ የተሰማራችሁ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ሁሉ ቀርባችሁ መወዳደር እንደምትችሉ እናሳውቃለን፡፡
1. የዘመኑን ግብር የከፈሉና የ2018 ዓ.ም ፍቃድ ያሳደሱ
2. በማሽን ኪራይ የንግድ ፈቃድ ያለው
3. የግብር መለያ ቁጥር /TIN/ ያለውና VAT ተመዝጋቢ የሆነ
4. TOT (3%) ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ
5. በማንኛውም የማሽን ብልሽት ጊዜ ባለቤቱ ባለሙያ ልኮ በራሱ ውጭ በሦስት ቀናት ውስጥ ማስጠገን የሚችል
6. ተወዳዳሪዎች የማሽኑን ስም፡ የማሽኑን ሞዴል፣ ማሽኑ የተመረተበት ዘመን፤ የማሽኑ ጉልበት፤ የማሽኑ ብዛት፣ የግል ወይም ኪራይ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
7. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ከሁሉም ዋጋ 2% ብር በጥሬ /CPO/ የባንክ ቼክ ከቴክኒካል ሰነድ ማስያዝ የሚችል፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ በተለያየ ፖስታ አሽጎ ማስገባት አለባቸው
9. የሥራ ሁኔታ ላይ ተመስርቶ ለማሽኑ የሚሠጥ ሥራ 20% ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል
10. አከራዩ ማሽኖቹን የማምጣትና የመመለስ ግዴታ አለበት፣ የምግብ እና የሰርቪስ ወጪ በተወዳዳሪ ድርጅት የሚሸፈን ይሆናል፤፤ የነዳጅ ወጪ ወረዳው በራሱ ወጪ ይሆናል፡፡
11. አሸናፊው ከተወዳደሩ መሐል ሁሉንም መስፈርት አሟልቶ ዝቅተኛ ዋጋ ያስገባ ይሆናል፡፡
12. የጨረታውን ሠነድ መግዣ የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሽህ) ለሊሙ ሠቃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
13. የጨረታው ሠነዱ የሚሸጠው ከመስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት በሊሙ ሰቃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ይሆናል፡፡
14. ሠነዱን የገዛ ተጫራች የገዛውን ሠነድ በተጠቀሰው መሠረት ሞልቶ እስከ ጥቅምት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 4:30 ድረስ ብቻ የምንቀበል ይሆናል፣ ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ውጭ የሚመጣ ተጫራች ማስተናገድ አይቻልም፣ ጨረታው የሚከፈተው ጥቅምት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሠዓት ላይ ተወዳዳሪዎች/ ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሊሙ ሠቃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ይሆናል ተጫራቾች/ተወዳዳሪዎች/ ሕጋዊ ወኪላቸው አለመገኘታቸው ጨረታው እንዳይከፈት አያደርግም፡፡
15. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡– ተወዳዳሪዎች ሠነዱን ከማሸጋቸው በፊት በሕጋዊ ማህተማቸው በማረጋገጥና በሰም በታሸገ አንቬሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 047 462 0008 / 047 462 0146 መደወል ይችላሉ።
በጅማ ዞን የሊሙ ሰቃ ወረዳ መንገድና ሎጀስቲክስ ጽ/ቤት