ሪፕል ኢፌክት ኢትዮጵያ በቀድሞ ስሙ ሴንድ ኤ ካው ኢትዮጵያ) የእንቁላል ጣይ ዶሮ ህጋዊ ፈቃድ ካላቸውና በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል


Reporter(Oct 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የእንቁላል ጣይ ዶሮ ግዢ ጨረታ

ሪፕል ኢፌክት ኢትዮጵያ በቀድሞ ስሙ ሴንድ ካው ኢትዮጵያ) እ.እ.አ 2006 ጀምሮ በኢትዮጵያ በዘላቂ ግብርና በእንሰሳት አያያዝ በተፈጥሮ ሃብት እንክብካቤ በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ቅነሳ እና መሰል የልማት ስራዎችን በመስራት ላይ የሚገኝ አለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው።

በመሆኑም በአሁን ሰዓት ድርጅቱ ከሲታር ባክስ ፋዉንዴሽን (Starbucks Foundation) ጋር በመተባበር በሲዳማ ክልል በቤንሳ ወረዳ የሚገኙ አነስተኛ የመሬት ይዞታ ባላቸው ቡና አብቃይ ሴት አርሶ አደሮችን አቅም ማጎልበት (Resilient and empowered women and girls) ለተባለዉ ፕሮጀክት ለተጠቃሚ አርሶ አደሮች የሚሆን የእንቁላል ጣይ ዶሮ ህጋዊ ፈቃድ ካላቸውና በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁ ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች የጨረታ ሰነዶቻችሁን ከታች በተጠቀሰው የድርጅቱ አድርሻ በማስገባት እንድትወዳደሩ ተጋብዛችሃል።

የጨረታ መደብ /Lot / 1 _ የእንቁላል ጣይ ዶሮ

ተ/ቁ

የዶሮ  ዓይነት

መለኪያ

ብዛት

የዝርያ ኣይነት

ምርመራ

 

ተጨማሪ የሚያስፈልገው ማስረጃዎች

 

የእንቁላል ጣይ

በቁጥር

5625

Sasso

ከበሽታ ነፃ የሆነ ቢያንስ ሁሉንም አስፈላጊ ክትባቶቹን የተከተቡ ማሬክስኒውካስል ጉምቦሮ፣ፋውል ፖክስ ኢንፌክሽየስ፣ ብሮንኪቲስ) ሁሉም ዶሮዎች በተመሳሳይ እድገት ደረጃ ላይ ያሉ ሆነው፣ ዕድሜያቸው 48 ቀን የሞላቸው የመላመድ ችሎታችው ሁሉንም የኢትዮጵያ አካባቢ የተላመደ፤ በአመት ቢያንስ 280 እንቁላል የሚሰጥ መሆን አለባችው።

የዝርያ ስምና ምንጭ የሚገልጽ መዝገብ፣ እና የክትባት መዝገብ ማረጋገጫ ያስፈልጋል።

 

 

  1. ተጫራቾች የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነትና 2018 ዓም የታደሰ የንግድ ፈቃድ ሊኖራቸው ይገባል።
  2. ተጫራቾች መወዳደር ለሚፈልጉት የጨረታ መደብ በፖስታ በማሸግና የጨረታ መደቡን ቁጥር በመጻፍ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረብያቸው ላይ ዋጋው ጸንቶ የሚቆይበትን ጊዜ፣ ቫት እና የትራንስፖርተሽን ወጪዎችን ማካተት አለማካተቱን መግለጽ ይጠበቅባችዋል።
  4. የጨረታ ማስገቢያ ፖስታው ላይ የጨረታው መደብና ቁጥር መግለጽ ይኖርበታል።
  5. ተጨራቾች በተጠየቁ ጊዜ ዋጋ ያስገቡለትን ዶሮ ለማሳየት ወይም ለማቅረብ ፈቃደኛ መሆን ይኖርባችዋል።
  6. ሪፕል ኢፌክት ኢትዮጵያ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻችሁን ከታች በተጠቀሰው የድርጅቱ አድራሻ ማስገባት ይኖርባችኋል።
  8. የጨረታ ማስገቢያ ጊዜ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 5 የስራ ቀናት ይሆናል።
  • የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ አድራሻ፡ ሪፕል ኢፈክት ኢንተርናሽናል ካሳንችስ ወረዳ 08 ከእሊሌ ሆተል ቀጥሎ SA ሕንጻ (ህብረት ባንክ ያለበ) 7ተኛ ፎቅ ስልክ ቁጥር (+251)-11-647-7233/34 አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ። ወይም

ማሳሰብያ፦

ሪፕል ኢፌክት ኢትዮጵያ

ቤንሳ ፕሮጀችት /ቤት

ቤንሳ፣ዳዬ ከተማ

ስልክ፡ +251 90 988 7698

ሁሉም ተጫራቾች የተጠቀሱትን ቴክኒክ መስፈርቶች መሟላትና አስፈላጊ ሰነዶችን ማቅረብ አለባቸው።

  • ያልተሞላ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውምየቀድሞ የእንቁላል ዶሮ አቅርቦት ተሞክሮ ያላቸው አቅራቢዎች እንዲወዳደሩ ይበረታታሉ።

 


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *