Your cart is currently empty!
በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃ መለዋወጫዎች እና ሌሎች እቃዎች በጨረታ አወዳደሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 24, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ ከታች በሰንጠረዥ የተገለፁትን ጥሬ ዕቃ መለዋወጫዎች እና ሌሎች እቃዎች በጨረታ አወዳደሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
|
የሎት ቁጥር |
የእቃው አይነት |
|
ሎት-1 |
ለተለያዩ የፕላስቲክ ማምረቻ የሚውሉ ግብዓቶች |
|
ሎት-2 |
የማሽን መለዋወጫዎች ኤሌክትሪካል ፓርቶች |
|
ሎት-3 |
የማሽን መለዋወጫ መካኒካል ፓርቶች |
|
ሎት_4 |
የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች |
|
ሎት-5 |
ለማሽን የሚያስፈልጉ ዘይትና ቅባት |
|
ሎት-6 |
የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያ |
|
ሎት-7 |
የፅዳት እቃዎች |
በመሆኑም ተጫራቾች፡–
1. በኢንዱስትሪው ሰፕላይ ቼን ማኔጅመንት ቡድን ቢሮ በመምጣት ዝርዝር መረጃ፣ የተጫራቾችን መመሪያ እና የዕቃዎችን ዓይነትና መጠን የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
2. በዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ ተጫራቹ የዕቃው ዋጋ በሚለው አምድ ስር የሚሸጡበትን የነጠላ ዋጋ በአሃዝ ያለስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቨሎፕ የኢንዱስትሪው ሰፕላይ ቼን ማኔጅመንት ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ማስገባት አለባችሁ።
3. ተጫራቹ የዕቃዎችን የተናጥል ዋጋ ማቅረብ ይኖርበታል።
4. ትክክለኛ የተጫራች ስምና አድራሻ በታሸገው ኤንቨሎፕ እና በመጫረቻ ሰነድ ላይ መገለፅ ይኖርበታል።
5. ተጫራቾች የእቃዎችን ለተቀመጠው የነጠላ ዋጋ ድምር የጨረታ መነሻ ዋጋ 2 በመቶ (2%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሳጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል። የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል።
6. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ዕለት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንዱስትሪው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም
7. ተጫራቾች የጨረታውን ውጤት በኢንዱስትሪው ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከወጣ ቀን ጀምሮ ቅሬታ ካላቸው በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በጽሁፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
8. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥራችን 0116670485/0118592286 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ላይ በየገጹ ስምና ፊርማ ማስገባት አለባቸው።
10. ተጫራቾች የቫት ሠርተፍኬት፣የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ ሠርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
11. ኢንዱስትሪው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻችን፦
በመገናኛ ወደ ገርጂ በሚወስደው መንገድ ከአምቼ ዝቅ ብሎ ኒያላ ሞተርስ ፊት ለፊት
በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ