Your cart is currently empty!
የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት በአይናምባ ክላስተር በብሄረሰብ ቋንቋ ትምህርት ስለሚማሩ ተማሪዎች መጽሐፍ ለማሳተም በጨረታ አወዳድሮ ለማሳተም ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 24, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት በአይናምባ ክላስተር በብሄረሰብ ቋንቋ ትምህርት ስለሚማሩ ተማሪዎች መጽሐፍ ለማሳተም በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለማሳተም ይፈልጋል። በዚህ መሠረት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፣
- በዘርፋ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል /የምትችል፣
- የዘመኑን ግብር የከፈለ/ለች እና ክሊራንስ ከግብር መ/ቤት ያቀረበ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን ነምበር) ማቅረብ የሚችል /የምትችል፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ እና ኮፒውን አያይዞ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዶች ጋር የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 40,000 (አርባ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- የታደሰ ህጋዊ ሰውነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በአሃዝ እና በፊደል መግለጽ ለለባቸው፡፡ በፊደል እና በሃዝ መካከል ልዩነት ካለው በፊደል የተገለጸው ይወሰዳል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ሶስት መቶ (300) በመክፈል ከደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10/አስር/ በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሻል አንድ(1) ኦርጅናል እና ሁለት(2) ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል አንድ(1) ኦርጅናል እና ሁለት(2) ኮፒ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን መግልጽ ይኖርባቸዋል፡፡ ያለበለዚያ ያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ፊርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ፖስታውን በደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢኮ/ል/ጽ/ል/ቤት ቢሮ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 21(ሃያ አንድ) ቀናት ክፍት ሆኖ በ21ኛው ቀን ከሰዓቱ 9:00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ከቀኑ 9:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፣ እለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
ማሳሳቢያ: ተጫራቾች የማህበሩ አባላት ስለመሆናቸው የስም ዝርዝር ከነ ሥራ ኃላፊነታቸው የሚገልጽ ከአደራጅ መ/ቤት ለደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢኮ//ጽ/ቤት አድራሻ የተጻፈ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
12. የግንባታ ዲዛይን የሚቀርብ ይሆናል
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- የደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት
ደ/ወርቅ ስልክ ቁጥር ፦ 09 66 88 69 73 / 09 10 99 77 47/ 09 29 24 17 31 በመደወል መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ።
የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት