የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በወረዳው ውሃና መስኖ ልማት ጽ/ቤት የሾር አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክት በመንገድ ሥራ ምክንያት ብልሽት ስላጋጠመው በዘርፉ በተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 24, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በወረዳው ውሃና መስኖ ልማት ጽ/ቤት የሾር አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክት በመንገድ ሥራ ምክንያት ብልሽት ስላጋጠመው በዘርፉ በተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፣
  2. ደረጃ 5GC/WWC-5/GWWC-5 እና ከዚያ በላይ የሆነ ድርጅት፣
  3. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል /የምትችል፣
  4. የዘመኑን ግብር የከፈለ ለች እና ክሊራንስ ከግብር መ/ቤት ያቀረበ፣
  5. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን ነምበር) ማቅረብ የሚችል /የምትችል፣
  6. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ እና ኮፒውን አያይዞ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፡፡
  7. የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል /የምትችል።
  8. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዶች ጋር የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በባንከ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ፡፡የታደሰ ህጋዊ ሰውነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
  9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በአሃዝ እና በፊደል መግለጽ አለባቸው፡፡ በፊደል እና በአሃዝ መካከል ልዩነት ካለው በፊደል የተገለጸው ይወሰዳል፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ሶስት መቶ (300) በመክፈል ከደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10/አስር/ በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሻል አንድ(1) ኦርጅናል እና ሁለት(2) ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካ አንድ(1) ኦርጅናል እና ሁለት(2) ኮፒ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  12. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡ ያለበዚያ ያቀረቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ተዳርጎ ይወሰዳል።
  13. ተጫራቾች በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ፊርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
  14. ተጫራቾች የጨረታ ፖስታውን በደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  15. ጨረታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21(ሃያ አንድ) ቀናት ክፍት ሆኖ በ21ኛው ቀን ከሰዓቱ 9:00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ከቀኑ 9፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፣ ለዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

ማሳሰቢያ፦

1. ተጫራቾች የማህበሩ አባላት ስለመሆናቸው የስም ዝርዝር ከነ ሥራ ኃላፊነታቸው የሚገልጽ ከአደራጅ መ/ቤት ለደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢኮ/ጽ/ቤት አድራሻ የተጻፈ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል።

2. የግንባታ ዲዛይን የሚቀርብ ይሆናል

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- የደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ደ/ወርቅ

ስልክ ቁጥር፡- 09 66 88 69 73 / 09 10 99 77 47/ 09 29 24 17 31 በመደወል መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ፣

የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *