Your cart is currently empty!
የሲዳማ ብ/ክ/መ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ የsupplay and installation for CCTV camera ግዥ እና የኔትወርክ መሰረተ-ልማት ዕቃ አቅርቦት፣ ዝርጋታ እና ለአውቶሜሽን ስራዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 24, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብ/ክ/መ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሎት የተገለጸውን ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1. የsupplay and installation for CCTV camera ግዥ፣
- ሎት 2. የኔትወርክ መሰረተ-ልማት ዕቃ አቅርቦት፣ ዝርጋታ እና ለአውቶሜሽን ስዎራች ግዥ፣
በመሆኑም ተጫራቾች፡-
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 200,000(ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ሲሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) እየከፈሉ ከመ/ቤቱ ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ) በጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው የቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ እና የፋይናንሺያል ሰነድ አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ ከ11ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሂሣብ ላይ ስማቸውንና፣ ፊርማቸውን፣ አድራሻቸውንና ስልክ ቁጥር ማስፈር አለባቸው፣
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 046-221-7014 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የመ ቤቱ አድራሻ ከሀዋሳ የሲዳማ ብ ክ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽቤት ጎን ይገኛል።
የሲዳማ/ብ/ክ/መንግስት ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ
cttx Art cttx, cttx Audio Visual, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Equipment cttx, cttx Installation, cttx IT and Telecom cttx, cttx Networking Equipment and Installation cttx, cttx Safety and Security cttx, Electromechanical and Electronics cttx, Maintenance and Other Engineering Services cttx, Photography and Filming Service and Equipment cttx