ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የጽሕፈት እቃዎችና ቶነሮች፣ የፅዳት እቃዎች እና የሕትመት ሥራዎችን ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 25, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ

የጨረታ ቁጥር L/OT/09/SlG/2018

ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ከዚህ በታች የተመለከቱትን እቃዎች፡

  • ሎት 1 የጽሕፈት እቃዎችና ቶነሮች፣
  • ሎት 2 የፅዳት እቃዎች እና
  • ሎት 3 የሕትመት ሥራዎችን ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ 2017/18 . የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፤ በተጨማሪም ተጫራቾች የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ወይም የሚመለከተው የመንግሥት አካል ባዘጋጀው የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።

2. ጨረታው ጥቅምት 26 ቀን 2018 .. ከቀኑ 800 ሰዓት ላይ ይዘጋል። ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በቁጥር 4 በተገለፀው አድራሻ በዕለቱ ከቀኑ 830 ሰዓት ላይ ይከፈታል ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ስነድ ውድቅ ይደረጋል።

3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል በተራ . 4 ከተመለከተው ቢሮ መግዛት ይችላሉ።

4. ጨረታው የሚገባበትና የሚከፈትበት አድራሻ ቀጥሎ የተመለከተው ነው።

ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ግዥና ንብረት አስተዳደር

ሜክሲኮ አካባቢ አልሣም ጨለለቅ ታወር ፊት ለፊት

ፊሊፕስ ሕንፃ 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220

... 20034-1000

ስልክ ቁጥር +251 11 551 61271/50 04 17

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

5. ተጫራቾች ለአገልግሎቱ የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/ ለሎት 2 25,000.00 / ሀያ አምስት ሺህ ብር/ እና ለሎት 3 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ በሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (ጋራንቲ) ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

6. የጨረታው ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ 60 ቀናት ነው።

7. የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ የመቆያ ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ 90 ቀናት ነው።

ግሩፑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ