Your cart is currently empty!
በምዕራብ ወለጋ ዞን የኖሌ ካባ ወረዳ ገንዘብ ጽህፈት ቤት ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዘመን ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች እና የተለያዩ ሞተር ሳይክል በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 25, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምዕራብ ወለጋ ዞን የኖሌ ካባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዘመን ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች እና የተለያዩ ሞተር ሳይክል በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
መስፈርት፡–
1. ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የ2018 ዓ.ም የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፤ ከሚመለከተው መ/ቤት የተመዘገበበት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡ መሆኑና ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
2. ያሸነፈበትን ዕቃ በተፈለገበት ጊዜ እስከ ኖሌ ካባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በራሱ ትራንስፖርት አምጥቶ ማስረከብ የሚችል፤
3. ተጫራቾች የተወዳደሩባቸው ዕቃዎች ሁሉ ጥራቱ የተጠበቀ መሆን አለበት፤ ጥራቱን ያልጠበቀ ዕቃ ካቀረበ መልሶ መቀየር አለበት አለበለዚያ ተቀባይነት አይኖረውም።
4. በወረዳው የገንዘብ ጽ/ቤት የገበያ ጥናት ተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ፈቃደኛ መሆን የሚችል።
5. ተወዳዳሪው ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም 10,000 (አስር ሺህ) ብር በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችል።
6.ተጫራቾች የተጠየቁትን ዕቃ ሁሉ ዋጋ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው። አለበለዚያ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል።
7. አሸናፊው ያሸነፈበትን ዕቃ ሁሉ በአንድ ላይ ውል በፈረመበት ጊዜ ውስጥ ማቅረብ አለበት። በተናጠል ካቀረበ (አጠቃሎ ሳይጨርስ) ገንዘቡ አይሰጠውም።
8. በአቅራቢዎች ምዝገባ የተመዘገበበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
የአቅራቢው ግዴታ፡–
1. የጨረታ ማስታወቂያ ሠነድ የማይመለስ 100 ብር (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በኖሌ ካባ ወረዳ ከገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 መግዛት የሚችል።
2. የጨረታ ሠነድ (የዕቃው ዝርዝር) ፋይናንስ ኦሪጅናልና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታ በማሸግ ሁለቱንም በአንድ ፖስታ በሰም በማሸግ የራሱን ፊርማና የድርጅቱን ማህተም አድርጎበት በታሸገ ኤንቨሎፕ የሚያቀርብ፤
3. የጨረታ ሠነድ ቴክኒክ ኦሪጅናልና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታ በማሸግ ሁለቱንም በአንድ ፖስታ በማሸግ የራሱን ፊርማና የድርጅቱን ማህተም አድርጎበት በታሸገ ኤንቨሎፕ የሚያቀርብ፤
4 አሸናፊው የውል ስምምነት ማስከበሪያ በመመሪያ መሠረት አሸናፊ ከሆኑ ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውሰጥ ከጠቅላላው ግዥ 10% በጥሬ ገንዘብ (በባንክ በተረጋገጠ ቼክ) ማስያዝ የሚችል።
5. ተጫራቾች ተወዳዳሪው ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የዕቃውን ናሙና ማቅረብ አለበት።
6. የጨረታ አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሠረት የጨረታው አሸናፊነቱ በጽሑፍ እንደ ተገለጸ እስከ 15 ቀን ውስጥ በኖሌ ካባ ገንዘብ ጽ/ቤት መጥቶ ውል መፈረም አለበት። ይህ ባይፈጸም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል።
7. የጨረታ አሸናፊ በአሸነፈበት ዕቃ ሁሉ የሁለት ወር ዋስትና መሰጠት የሚችል።
የጽ/ቤቱ መብት፡–
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።
- ጨረታው የሚጠናቀቅበትና የሚከፈትበት ቀን፡–
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት ብቻ ይቆያል።
- ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የሥራ ቀናት በኖሌ ካባ ገንዘብ ጽ/ቤት በመቅረብ መግዛት የሚችሉና ተወዳዳሪዎች (ወኪሎቻቸው) በተገኙበት ቦታ በ16ኛ ቀን በ4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል። ሆኖም ቀኑ በዓል/በእረፍት ቀን ላይ ከዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን ይከፈታል።
- ለተጨማሪ መረጃ በሚከተሉት የስልክ ቁጥሮች ሊጠይቁ ይችላሉ።
0917354411/0979579290
በምዕራብ ወለጋ ዞን የኖሌ ካባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት