Your cart is currently empty!
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ዞን የሀብሩ ወረዳ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት የግዥ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ለሀብሩ ወረዳ ሴ/መ/ቤቶች በመደበኛ በጀት የመኪና ዕቃ መለዋወጫ፤ የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃ፣ የመኪና ጎማ ግዥ በዘርፉ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸውን አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 26, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ዞን የሀብሩ ወረዳ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት የግዥ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ለሀብሩ ወረዳ ሴ/መ/ቤቶች በመደበኛ በጀት የመኪና ዕቃ መለዋወጫ ፤ የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃ ፣ የመኪና ጎማ ግዥ በዘርፉ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸውን አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆን ይጋብዛል፡፡
1.የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው በተጠየቁት የግዥ አይነትና ዘርፍ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ::
2.የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው
3.የግዥ መጠኑ ከብር 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ፡፡
4.በውሉ መሰረት ያሸነፈበትን እቃ ግዥ ኦርጅናል እቃዎች ማቅረብ የሚችል ፡፡
5.ማስታወቂያው አየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ለሀብሩ ወረዳ ሴ/መ/ቤቶች በመደበኛ በጀት የመኪና ዕቃ መለዋወጫ ፤ የጽህፈት መሳሪያ ፡የጽዳት እቃ እና የመኪና ጎማ ግዥ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ 11፡30 የስራ ቀን ድረስ ብቻ ነው፡፡
6.የጨረታውን ማስከበሪያ ለመኪና ዕቃ መለዋወጫ 25,000/ሀያ አምስት ሺህ ብር/፣ ለጽህፈት መሳሪያ 20,000/ ሀያ ሺህ ብር/፣ ለጽዳት እቃ 8000/ስምንት ሺህ ብር/፣ ለመኪና ጎማ 14,000/አስራ አራት ሺህ ብር/ በCPO ያስያዙ ወይም ገንዘቡን አስቀድሞ ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ኮፒ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ያቀርባሉ፡፡
7.ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድና መመመሪያ ለእያንዳንዱ ለተጠየቀ ግዥ ሰነድ በማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን ዝርዝር ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሰዓት ጨረታውን አየር ላይ ከዋለበት እስከ መጨረሻ ቀን እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 12 በመገኘት መግዛት ይችላሉ፡፡
8.ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት ለሀብሩ ወረዳ ሴ/መ/ቤቶች በመደበኛ በጀት የመኪና ዕቃ መለዋወጫ ፤ የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃ እና የመኪና ጎማ ግዥ በ16ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 12 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል ::
9.የጨረታ ሳጥኑ በ4፡05 ሰዓት ይታሸጋል፡፡ የጨረታው ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
10.የጨረታ ሳጥን የሚከፈትበት ቦታ ግዥ/ን/ብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 12 ለሀብሩ ወረዳ ሴ/መ/ቤቶች በመደበኛ በጀት የመኪና ዕቃ መለዋወጫ ፤ የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃ ፣ የመኪና ጎማ ግዥ በ16ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ራሳቸው ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት እለት የስራ ቀን ካልሆነ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ የሚከፈት ይሆናል፡፡
11.ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ ከሆኑ 10% የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተረጋገጠ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርብዎታል፤
12.መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
13.በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 12 ድረስ በአካል በመገኘት ማግኘት ይችላሉ፡፡
14.አሸናፊው የሚለየው በሎት ድምር ውጤት መሰረት ይሆናል፡፡
የሀብሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት