በሀገር መከላከያ ሚ/ር የ605ኛ ኮር ጠ/መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ለኮሩ አገልግሎት የሚውሉ የጽሕፈት፣ የሥልጠና መርጃ እና የፅዳት ዕቃዎች፣ የቀላል ተሽከርካሪ፣ የማሽነሪ እና የጀነሬተር መለዋወጫ ዕቃዎች በዘርፉ ከተሰማሩ ሕጋዊ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 28, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ

የ605ኛ ኮር ግ/ጨ/ቁጥር 01/2018 ዓ/ም

በሀገር መከላከያ ሚ/ር የ605ኛ ኮር ጠ/መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ለኮሩ አገልግሎት የሚውሉ፡-

  1. የጽሕፈት የሥልጠና መርጃ እና የፅዳት ዕቃዎች
  2. የቀላል ተሽከርካሪ፣ የማሽነሪ እና የጀነሬተር መለዋወጫ ዕቃዎች ሲሆኑ በዘርፉ ከተሰማሩ ሕጋዊ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን። በዚህ መሠረት በዘርፉ የተሰማሩበት የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የዘመኑ ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ፍቼ 605ኛ ኮር ጠቅላይ መምሪያ በሚገኘው ግዥ ክፍል ቢሮ በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ። ጨረታው በተከታታይ 10 ቀናት አየር ላይ ውሎ ጥቅምት 27 ቀን 2018 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ፍቼ ሪፈራል ሆስፒታል ፊት ለፊት አንበሳ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የ605ኛ ኮር ጠቅላይ መምሪያ ግዥ ክፍል ይከፈታል። መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

  • ለበለጠ መረጃ 0911783286 ወይም 0920036840 ወይም 0923536151

በሀገር መከላከያ ሚ/ር የ605ኛ ኮር ጠ/መምሪያ ግዥ ክፍል


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *