የቀወት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የጽህፈት መሳሪያ፣ የመኪና ጎማ፣ የኤሌክትሮኒክስ እና የህንፃ መሳሪያ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 27, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ

ቁጥር 02/2018

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰ/ሸዋ ዞን የቀወት ወረዳ ገንዘብ /ቤት ለቀወት ወረዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል እቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡

  • ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ የጨረታ ማስከበሪያ ( ሲፒኦ ብር 20,000)
  • ሎት2. የመኪና ጎማ የጨረታ ማስከበሪያ ( ሲፒኦ ብር 30,000)
  • ሎት3. የኤሌክትሮኒክስ እቃ የጨረታ ማስከበሪያ ( ሲፒኦ ብር 30,000)
  • ሎት4. የህንፃ መሳሪያ የጨረታ ማስከበሪያ ( ሲፒኦ ብር 15,000)

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN/ ያላቸው
  3. በጨረታው ላይ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የግዥው መጠን ከብር 200000 በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑበት ሰርተፍኬት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  4. ተጫራቾች ከ1-3 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው።
  5. በጨረታው ላይ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታው ውድድር በጥቅል መሆኑን አውቀው ጨረታውን መሙላት ይጠበቅባቸዋል።
  6. ተጫራቾች ከላይ በተገለፀው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
  7. ማንኛውም ተጫራቾች ከላይ በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያው የጨረታ ሰነዱ ጸንቶ ከሚቆይበት 40 ቀን በኋላ ለተጨማሪ 20 ቀን ጸንቶ የሚቆይ መሆኑን አውቀው የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  8. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200 በመከፈል ከቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይችላሉ።
  9. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዛው እለት ከጠዋቱ 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ጨረታ የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
  10. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 33-664-1612 ማግኘት ይችላላሉ።

በሰ/ሸዋ ዞን የቀወት ወረዳ ገንዘብ /ቤት