Your cart is currently empty!
በአሪ ዞን ጂንካ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት ለጂ/ከ/አስተዳደር የማዘጋጃ ቤት የዶዘር ማሽን መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም እና ጥገና ለማስደረግ ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 27, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
በአሪ ዞን ጂንካ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት ለጂ/ከ/አስተዳደር የማዘጋጃ ቤት የዶዘር ማሸን መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም እና ጥገና ለማስደረግ ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር ከፍለው ያጠናቀቁ እና የንግድ ፈቃዳቸውን ያደሱ መሆን ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት የጂ/ከ/አስ/ፋ/ጽ/ቤት የግዥ ስራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ 500 /አምስት መቶ ብር / በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች የንግድ ፈቃድ ምስክር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የቫት ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት፣ ከጨረታ ሰነዱ ጋር የሰነዱን አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ዶክመንታቸውን ኦሪጅናሉን ከኦርጅናሉ ጋር ኮፒውን ከኮፒው ጋር በማድረግ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን CPO 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። በጂንካ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ጽ/ቤት ስም ከታወቀ ወይም ስልጣን ከተሰጠው አካል የጨረታ ማስከበሪያ በማዘጋጀት ከጨረታው ዶክመንት ጋር በማስገባት ማስያዝ አለባቸው።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ኦሪጅናል ዶክመንታቸውን ይዘው መቅረብ አለባቸው። አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸው ስራዎች ለመፈፀም ያሸነፉበት ገንዘብ 10% ሲያስዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማሉ። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ወይም ቀኑ በስራ ቀን ላይ ካልዋለ በማግስቱ የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡–መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።ጨረታ በሚከፍትበት ወቅት የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጎለውምል።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 046-775-0256 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በአሪ ዞን የጂ/ከ/ፋ/ጽ/ቤት