በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት በተለያዩ ወረዳዎች ለሚያሠራቸው የግንባታ ሥራዎች በኮንስትራክሽን ዘርፍ ብቃት ያላቸው አማካሪዎችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል

Addis Zemen(Oct 29, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.

የግንባታ አማካሪ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር LSCDCWO/NCB/003/2018

በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት በተለያዩ ወረዳዎች ለሚያሠራቸው የግንባታ ሥራዎች በኮንስትራክሽን ዘርፍ ብቃት ያላቸው አማካሪዎችን አወዳድሮ ማሠራት ስለሚፈልግ በጨረታው መሳተፍ ለሚፈልጉ የግንባታ አማካሪዎች ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ የተሟላ የሰው ኃይል እና በኮንስትራክሽን ዘርፍ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች ማቅረብ የሚችሉ፤ በተጨማሪም ከታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይቻላሉ፡፡

ሎት

የሚያማክሩት ፕሮጀክቱ ስም

የሚገኙበት ወረዳ

የአማካሪዎች ደረጃ

የጨረታ ሰነድ የሚሸጥበት ቀን

የጨረታ ሰነድ የሚመለስበት ቀንና ሰዓት

ጨረታው የሚዘጋበት ቀን እና ሰዓት

ጨረታው የሚከፈትበትን ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ

1

የወረዳ 5 ጤና ጣቢያ ጂ+4 ግንባታ ሥራ

3

ደረጃ 4 እና በላይ

ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት

ከወጣበት 22ኛው የሥራ ቀን በ22ኛው የሥራ ቀን ከ3፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት

ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ22ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት

በወጣበት 22ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት በክ/ከተማው 5ኛ ፎቅ 

2

የወረዳ 1 መስከረም 1 አፀደ ሕፃናት ጂ+4  ግንባታ ሥራ

9

ደረጃ 4 እና በላይ

ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት

ከወጣበት 22ኛው የሥራ ቀን በ22ኛው የሥራ ቀን ከ3፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት

ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ22ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት

በወጣበት 22ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት በክ/ከተማው 5ኛ ፎቅ 

3

የወረዳ 3 ህዳሴ ፍሬ ጤና ጣቢያ ጂ +4 ግንባታ ሥራ

5

ደረጃ 4 እና በላይ

ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት

ከወጣበት 22ኛው የሥራ ቀን በ22ኛው የሥራ ቀን ከ3፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት

ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ22ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት

በወጣበት 22ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት በክ/ከተማው 5ኛ ፎቅ 

4

የወረዳ 3 አፍሪካ ብርሃን አፀደ ሕፃናት ጂ+4 መማሪያ ክፍሎች ግንባታ ሥራ

5

ደረጃ 4 እና በላይ

ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት

ከወጣበት 22ኛው የሥራ ቀን በ22ኛው የሥራ ቀን ከ3፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት

ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ22ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት

በወጣበት 22ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት በክ/ከተማው 5ኛ ፎቅ

5

የወረዳ 9 ቅዱስ ጊዮርጊስ አፀደ ሕፃናት ጂ+4 ግንባታ ሥራ

5

ደረጃ 4 እና በላይ

ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት

ከወጣበት 22ኛው የሥራ ቀን በ22ኛው የሥራ ቀን ከ3፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት

ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ22ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት

በወጣበት 22ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት በክ/ከተማው 5ኛ ፎቅ 

6

የወረዳ 10 ፍሬ ሕይወት አፀደ ሕፃናት ጂ+4 ግንባታ ሥራ

5

ደረጃ 4 እና በላይ

ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት

ከወጣበት 22ኛው የሥራ ቀን በ22ኛው የሥራ ቀን ከ3፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት

ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ22ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት

በወጣበት 22ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት በክ/ከተማው 5ኛ ፎቅ 

7

የወረዳ 9 ሱቆች ግንባታ ሥራ

9

ልዩ 1

ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት

ከወጣበት 22ኛው የሥራ ቀን በ22ኛው የሥራ ቀን ከ3፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት

ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ22ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት

በወጣበት 22ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት በክ/ከተማው 5ኛ ፎቅ 

8

የችግኝ ጣቢያ ግንባታ ሥራ

8

ልዩ 1

ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት

ከወጣበት 22ኛው የሥራ ቀን በ22ኛው የሥራ ቀን ከ3፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት

ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ22ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት

በወጣበት 22ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት በክ/ከተማው 5ኛ ፎቅ 

9

የአደጋ ስጋት መጋዘን ግንባታ ሥራ

ልዩ 1

ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት

ከወጣበት 22ኛው የሥራ ቀን በ22ኛው የሥራ ቀን ከ3፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት

ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ22ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት

በወጣበት 22ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት በክ/ከተማው 5ኛ ፎቅ 

10

የወረዳ 3 የአለሙ ሜዳ ስፖርት ሜዳ ግንባታ ስራ

3

ልዩ 1

ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት

ከወጣበት 22ኛው የሥራ ቀን በ22ኛው የሥራ ቀን ከ3፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት

ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ22ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት

በወጣበት 22ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት በክ/ከተማው 5ኛ ፎቅ 

 የምህንድስና ማማር ስራ አገልግሎት መስፈርቶች

  1. በጨረታው መሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለሥራው ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ብቻ፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው፣ ከፌዴራል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚ/ር ጊዜው ያላለፈው ማለትም ጨረታው ሲገባ የእድሳት ጊዜው ያላለፈው የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ቢሮ ጊዜው ያላለፈው ማለትም ጨረታው ሲገባ የእድሳት ጊዜው ያላለፈው የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው/ ከሁለቱም/ ፤ የአቅራቢነት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡ በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት ሥራ ላላቸው አማካሪዎች ደግሞ ያላቸው የግንባታ አፈፃፀም ከ75% በላይ መሆኑን የሚገልፅና መልካም አፈፃፀም (Good Performance) ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ከላይ የተጠቀሰውን ፕሮጀክት መግዛት ለምትፈልጉ ተጫራቾች ጨረታውን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው ቀን ውስጥ በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት 5ተኛ ፎቅ ላይ በመቅረብ ከሎት-1 እስከ 6 ለምትወዳደሩ ተጫራቾች የማይመለስ አምስት መቶ ብር (500ብር) በመክፈልና የድርጅታቸውን ማህተምና ፍላሽ ይዘው በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡ ከሎት-7 እስከ 10 ለምትወዳደሩ ተጫራቾች ከተደራጃችሁበት መንግሥታዊ ተቋም የዋስትና ደብዳቤ አፅፋችሁ በመያዝና የድርጅታቸውን ማህተምና ፍላሽ ይዘው በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲመልሱ አንድ ዋና (original) እና ሁለት ቅጂ (copy) የፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ አንድ ዋና (original) እና ሁለት ቅጂ (copy) የቴክኒካል 1 የጨረታ ሰነድ በተለያየ ኤንቨሎፕ በማዘጋጀትና በማሸግ የፋይናንስና የቴክኒካል ሰነድ በሁለት የተለያየ እናት ኤንቨሎፕ በማሸግ በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሕንፃ 5ተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የጽ/ቤቱ ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  4. ጨረታው በዚሁ በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር 5ተኛ ፎቅ በሚገኘው የጽ/ቤቱ ቢሮ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከማስገባታቸው በፊት የተጫራቾች መመሪያን  (instruction to bidders and scope of consultancy services) እነዲያነቡ ይመከራል፡፡
  6.  ከሎት-1 እስከ ሎት 6 ለምትወዳደሩ ተጫራቾች 50,000 ብር (ሃምሳ ሺ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (bid bond or bid security) ወይም በባንክ ትዕዛዝ ሲፒኦ (cpo) በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (UNCONDITIONAL BANK GUARANTEE) ከታወቀ ባንክ በልደታ ክፍለ ከተማ የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት ስም በማሠራት በኤንቨሎፕ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ከሎት-7 እስከ 10 ለምትወዳደሩ ተጫራቾች ከተደራጃችሁበት መንግሥታዊ ተቋም የዋስትና ደብዳቤ በልደታ ክፍለ ከተማ የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት ከም አፅፋችሁ በኤንቨሎፕ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7.  ከአንድ ሎት በላይ መወዳደር ከተወዳዳሪነት ሁሉም ላይ ያሰርዛል በተጨማሪም ተጫራቾች ሞልተው ያቀረቡት ሰነድ በሁሉም ገጾች ላይ ማህተም እና ፊርማ አለማድረግ፤ የሥራ ዝርዘር ዋጋ (rate) ላይ የማይነበብ እና ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ ካለ፤ ዋጋ (rate) ያልተሞላበት የሥራ ዝርዝር እንዲሁም የሥራ ዝርዝር ዋጋ (rate) ላይ ፍሉድ መጠቀም ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል፡፡
  8. ከሎት 1 እስከ ሎት 10 ለሚወዳደሩ የአማካሪ ድርጅቶች የዲዛይን ዝግጅት እና የሥራ ዝርዝር የማዘጋጀት ሥራ ይሠራል፡፡
  9.  ከሎት 1 እስከ ሎት 6 ለሚወዳደሩ የአማካሪ ድርጅቶች ከዲዛይን ዝግጅት በፊት የግንባታ ቦታው አፈር ምርመራ አድርገው የአፈር ምርመራውን ውጤት ያቀርባሉ፡፡
  10. የጨረታውን መመሪያ አለማክበር እና ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች አለማሟላት ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል፡፡
  11. የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በልደታ ክፍለ ከተማ የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ መረዳት ይቻላል፡፡
  12. አድራሻ፡- በልደታ ክፍለ ከተማ እስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት 5ተኛ ፎቅ ላይ መሆኑን አንገልጻለን፡፡
  13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ተስፋ ኮከብ ት/ቤት ጎን ልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አዲሱ ሕንጻ ላይ

አምስተኛ ፎቅ በዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት የምህድስና ግዥ ቡድን ክፍል፤

ደታ ክፍ ከተማ አስተዳደር  ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *