Your cart is currently empty!
በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ሲዝ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት የጽህፈት መሳሪያ፣ የኤሌክትሮኒክስ፣ የቧንቧ መለዋወጫ ዕቃዎች እና ልዩ ልዩ የእንስሳት መድሃኒቶችን በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ በማውጣት ግዢ መፈጸም ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 29, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ሲዝ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ልዩ ልዩ የግዢ አይነቶች በሎት በመከፋፈል ለአቅራቢዎች በሚመች ሁኔታ የተዘጋጀ መሆኑን እየገለጽን፡፡
- በሎት 1 (አንድ ) የጽህፈት መሳሪያ፣
- በሎት 2 (ሁለት) የኤሌክትሮኒክስ፣
- በሎት 3 (ሦስት ) የቧንቧ መለዋወጫ ዕቃዎች፣
- በሎት 4 (አራት ) ልዩ ልዩ የእንስሳት መድሃኒቶችን ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ በማውጣት ግዢ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በዘርፉ የተሰማሩትን አቅራቢ ድርጅቶች ከዚህ በታች በተዘረዘሩትን የመወዳደሪያ መስፈርቶች መሰረት እንድትወዳደሩ የሲዝ ከ/አስ/ር ፋ/ጽ/ቤት ጥሪ ያቀርባል፡፡
የመወዳደሪያ መስፈርት፡-
- በዘርፉ የተሰጠ ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ፣
- የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣
- የጨረታ ማስከበሪያ የ10,000 (አስር ሺህ ብር) ሲፒኦ ከታወቀ ባንክ ወይም ኢንሹራንስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በጨረታ አሸናፊ ለሚሆኑበት የጽህፈት መሳሪያ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቧንቧ መለዋወጫ ዕቃዎች እንዲሁም የእንስሳት መድሃኒቶች በጨረታው ያሸነፉበትን የጠቅላላ ገንዘብ መጠን 10% ውል ከመፈራረማቸው በፊት የውል ማስከበሪያ ከታወቀ ባንክ ወይም ኢንሹራንስ ለማስያዝ ፈቃደኛ የሚሆኑ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሚሆኑ አቅራቢ ድርጅቶች መ/ቤቱ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተመረጡ እቃዎች ላይ ናሙና እንዲቀርብለት የገለፃቸውን የዕቃ ዓይነቶች ናሙና ማቅረብ ግዴታ አለባቸው
- አሸናፊ ድርጅቶች ለሚያሸንፉብት የዕቃ ዓይነቶች ባቀረቡት ናሙና መሰረት ደረጃውን የጠበቀ ዕቃዎችን የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው ለ15 ተከታታይ ቀናቶች በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ከቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕስቱ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው ባሉበት በፋይናንስ ጽ/ቤት በግዢ ኬዝ ቲም ቢሮ ቁጥር- 05 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ሞልተው ሲመልሱ የፋይናንሺያል አንድ ኦረጅናል እና ሁለት ኮፒ እንዲሁም የቴክኒካል አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ማስረጃዎችን ለየብቻ በማሸግ _ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም በማድረግና ሁሉም ሰነዶች ላይ በመፈረም ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 05 ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተወዳዳሪዎች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ከሲዝ ከተማ አስ/ር ገቢዎች ጽ/ቤት የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ)ብር በመከፈል ማገኘት ይችላሉ፡፡
- ተወዳዳሪ ድርጅቶች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ የንግድ ፈቃድ እና አቅራቢነት የምስክር ወረቀት ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0477-77-06-20 ወይም 09-11-45-27-13 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሲዝ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ፅ/ቤት
cttx Building and Finishing Materials cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Construction and Water Works cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Health Care, cttx IT and Telecom cttx, cttx Office Machines and Accessories cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Plastic Products cttx, cttx Plastic Raw Materials and Products cttx, cttx Sanitary and Ceramics cttx, cttx Stationery cttx, cttx Veterinary Equipment and Supplies cttx, cttx Water Pipes and Fittings cttx, Electromechanical and Electronics cttx, Medical Industry cttx