Your cart is currently empty!
በጋም ሕ/ብ/ክ/መንግስት ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በጋምቤላ ከተማ የኅዳር 29 መሰብሰቢያ ኣዳራሽ ህንጻ ዕድሳት ለማከናወን በግንባታ ሥራ ተቋራጭ የብቃት ማረጋገጫ ደረጃ BC-3/GC-3 እና ከዚያ በላይ ያሉትን የሥራ ተቋራጮች በማወዳደር ማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 30, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የጨረታ ማስታወቂያ
በጋም ሕ/ብ/ክ/መንግስት ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በጋምቤላ ከተማ የኅዳር 29 መሰብሰቢያ ኣዳራሽ ህንጻ ዕድሳት ለማከናወን በግንባታ ሥራ ተቋራጭ የብቃት ማረጋገጫ ደረጃ BC-3/GC-3 እና ከዚያ በላይ ያሉትን የሥራ ተቋራጮች በማወዳደር ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፣
- የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሠርተፍኬት ያለው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣
- ከውዝፍ ግብር ነፃ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፣
- የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር( ቲን ነምበር) ያለው፤
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ14 ተከታታይ የሥራ ቀናት ተጫራቾች ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሠነድ የማይመለስ 1500.00/ አንድ ሺህ አምሰት መቶ / ብር በመክፈል ከክልሉ ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን መሪ ክፍል በመቅረብ መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዋስትና ማስከበሪያ 600,000 ብር (ስድስት መቶ ሺህ) ብር በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ ብቻ ከጨረታ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ዕድሳቱን የሚያከናውኑበትን ዋጋ ዋናውንና ኮፒ ሁለት /2/ እና ካምፓኒ ፕሮፋይል ዋናውንና ኮፒ ሁለት /2/ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በ15ተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30-4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ አስገብተው በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ላይ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በክልሉ ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን መሪ ክፍል ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በመሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር: +251-93 515 5382 ይጠቀሙ።
የጋም/ሕ/ብ/ክ/መንግስት ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ
ጋምቤላ