ዘመን ባንክ አ.ማ. በመያዣነት የያዘውን ንብረት ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Reporter(Jan 25, 2026)

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ

ዘመን ባንክ አ.ማ ብድር ሲሰጥ በመያዣነት የያዘውን ከዚህ በታች የተመለከተውን ንብረት ባለበት ሁኔታ(AS IS) በአዋጅ ቁጥር 97/1990(እንደተሻሻለው) በተሰጠው ስልጣን መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

የተበዳሪው ስም

 

የአስያዡ ስም

የንብረቱ አድራሻ

ቦታው ስፋት በሜትር ካሬ

የካርታ ቁጥር

የንብረቱ ዓይነት

 

የሐራጅ መነሻ ዋጋ

 

ሐራጅ የሚከናወንበት

ከተማ

ወረዳ

የቤት.

ቀን

የምዝገባ ሰዓት

የጨረታ ሰዓት

አዲስአለም አግሪካልቸራል ዴቨሎፕመንት .የተ.የግ.ማህበር

 

ተበዳሪው

ኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ ሸዋ ዞን፣ ሞጆ ከተማ

02

 

አዲስ

 

27,929 .ካሬ

 

6443/2011

 

የከብት ማድለቢያ እና የመኖ ማምረቻ ህንጻዎች

 

ብር 21,833,132.95 (ሃያ አንድ ሚሊዮን ስምንት መቶ ሰላሳ ሦስት አንድ መቶ ሰላሳ ሁለት ብር 95/100)

የካቲት 25 ቀን 2018 .

 

 

ጠዋት 4:00-5፡00

ጠዋት 5፡00-5፡50

 

የሐራጅ ደንቦች፡-

1. ተጫራቾች የንብረቱን የመነሻ ዋጋ (1/4) (አንድ አራተኛ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ በዘመን ባንክ ኢማ ስም በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።

2. አሸናፊው የሚለየው በደብዳቤ ሲገለጽ ነው::አሸናፊው አሸናፊነታቸው በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ አጠቃለው መክፈል አለባቸው::ይህንን ካላደረጉ ያስያዙት ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፣ እንደገና ጨረታው ይካሄዳል፣ የዋጋ መቀነስ ከተከሰተ አግባብነት ባላቸው ህጎች መሰረት ልዩነቱን የመጀመሪያው አሸናፊ እንዲከፍሉ ይጠየቃሉ።

3. ጨረታው በሚካሄድበት አዳራሽ ውስጥ መገኘት የሚችሉት ሲፒኦ ያስመዘገቡ ተጫራቾች ብቻ ናቸው።

4. ንብረቱን አስመልክቶ ማንኛውንም ለመንግስት ሊከፈል የሚገባውን ክፍያ የንብረት ግብር፤ ውዝፍ ሊዝ ክፍያ፣ በአካባቢው ላለው የልማት ማህበር ያልተከፈሉ ክፍያዎች ወዘተ ካሉ እነዚህን ክፍያዎች በሙሉ በጨረታው አሸናፊ የሚከፈል ይሆናል።

5. የሐራጅ ሂደቱ ከተጀመረ በኃላ ማንም ተጫራች መውጣት እና መግባት አይፈቀድም፣ ተጫራቹ ሳይፈቀድለት ማናቸውንም ዓይነት ንግግር ማድረግ አይችልም:: ይህንን ደንብ የማያከብር እና ጨረታውን የሚያውክ ተጫራች ካለ እንዲወጣ ተደርጎ ጨረታው በቀሩት ተጫራቾች ይቀጥላል።

6. የባንኩን የብድር ፖሊሲ እና ሥነሥርአት ለሚያሟሉ ተጫራቾች የንብረቱን የሐራጅ መነሻ ዋጋውን መጠን በከፊል የሚሸፍን ብድር ባንኩ ሊያመቻች ይችላል:: ባንኩ ብድሩን በማናቸውም ሁኔታ ለአሸናፊው ባይፈቀድ/ባይሰጥ አሸናፊው በዚህ የሐራጅ ደንብ ተ.ቁ 2 ላይ የተቀመጠውን ግዴታ እና ሌሎች ግዴታዎችን አያስቀርላቸውም።

7. ባንኩ ንብረቱን በገዥው ስም እንዲዞር ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል:: ከስም ዝውውር ጋር ያሉ ማናቸውንም ክፍያ ገዥው ይከፍላል::

8. የሐራጅ ሽያጩ የሚከናወነው ሞጆ ከተማ በሚገኘው የባንኩ ቅርንጫፍ ላይ ነው::

9. ባንኩ በሚያወጣው የጉብኝት ፕሮግራም መሰረት ተጫራቾች የሚሸጠውን ንብረት መጎብኘት ይችላሉ::

10. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-6-68 62 16 ወይም 0911152490 ወይም 0911456203 ወይም 0919 60 26 48 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::

11. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ዘመን ባንክ አ.ማ. Mexico, Ras Abebe Aregay Street, P.O.Box 1212 Addis Ababa, Ethiopia


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *