Your cart is currently empty!
በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሸገር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለፈርኒቸር ስራ የሚያገለግል የቪነር መለጠፍያ ማሽን (Edge Banding Machine) በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Jan 27, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 06/2018
ድርጅታችን ለፈርንቸር ስራ የሚያገለግል የቪነር መለጠፍያ ማሽን (Edge Banding Machine) በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም፣ተጫራቾች የማይመለስ 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመከፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት የሚችሉ ሲሆን ተጨራቾች ማሟላት የሚገባቸው፡-
- በዘርፍ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እና የሥራ መለያ ቁጥር ቲን ቁጥር ያላቸውና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾቹ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመኖራቸው የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የቪነር መለጠፍያ ማሽን (Edge Banding Machine) በተጠየቀው እስፔስፊክሽን መሠረት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ጨረታ ለመወዳደር የሚያስችል ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።
- እሸናፍው ተጫራች ስለ ማሽኑ አጠቃቀም ስልጠና የመስጠትና የመትከል ግደታ አለበት።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% በባንክ በተረጋገጠ በሲፒኦ በድርጅቱ ስም ማስያዝ ይኖርበታል።
የጨረታ ሠነዱን ለቡ መብራት ኃይል ሮያል ከረሜላና ቸኮሌት ፋብሪካ ህንጻ 3ተኛ ፎቅ ላይ ከሚገኘው ቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን ከሰኞ እስከ አርብ በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ። ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ 16 ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ በ4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል።መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል መሰረዝ ይችላል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0912131795 /0912080221 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሸገር
ቅርንጫፍ ጽ/ቤት