Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተሽከርካሪ ዘይቶች ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለሁለት ዓመት በማዕቀፍ ስምምነት ውል ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል
Addis Zemen(Jan 26, 2026)
በድጋሚ የወጣ የጨረታ
ማስታወቂያ ቁጥር EEP/NP/NCB/FA/01/2018
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተሽከርካሪ ዘይቶች ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለሁለት ዓመት በማዕቀፍ ስምምነት ውል ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ እና በግዥ ኤጀንሲው ድህረ ገጽ (eGP) የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ መሆን አለባቸው።
2. በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል።
3. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታ ብረት ፊት ለፊት በሚገኘው ዋና መ/ቤት ሕንፃ ቁጥር-11 1ኛ ፎቅ በሚገኘው ገንዘብ ተቀባይ ቢሮ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ) በመክፈል እና የጨረታ ሰነዱን ሕንፃ ቁጥር 9 1ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 201 በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።
4. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከተውን የተሽከርካሪ ዘይቶች አቅርቦት ግዥ የቴክኒካል እና የፋይናንሻል ሰነዳቸውን ለየብቻ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/NP/ NCB/FA/01/2018 የሚል ምልክት በማድረግ ከታች በተቀመጠው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
|
No |
Description |
የጨረታ ዋስትና /ማስከበሪያ |
የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
. ENGINE OIL # 40, . ENGINE OIL # 30, GEARBOX OIL # 90, and HYDRAULIC OIL 10w, |
230000 (ሁለት መቶ ሠላሳ ሺህ ብር ከ00/100
|
የካቲት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
|
የካቲት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
|
5. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-558-0627 መደወል ይችላሉ።
6. ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል