Your cart is currently empty!
በሸገር ከተማ የሰበታ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በሕጋዊ ኤጀንሲ የጥበቃ ሠራተኞችን በተለያየ የውሃ ጉድጓድ ጣቢያ በጨረታ አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል
Addis Zemen(Jan 27, 2026)
ለ3ኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሸገር ከተማ የሰበታ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በሕጋዊ ኤጀንሲ የጥበቃ ሠራተኞችን በተለያየ የውሃ ጉድጓድ ጣቢያ በጨረታ አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ተመዝጋቢ የሆኑ
3. ኤጀንሲው ከላይ የተጠቀሱትን የሚገልፅ ማስረጃዎች ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒውን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፤
4. ኤጀንሲው የጨረታው ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት/15/ተከታታይ የስራ ቀናት በስራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል 9 ቁጥር ገቢዎች ዳይሬክቶሬት ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
5. ኤጀንሲው የሚያቀርቡበትን የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር(ሰነድ) እና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ /በፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 (ሰባት ) ተከታታይ የስራ ቀናት በሸገር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የሰበታ ከተማ ቅርንጫፍ ባዘጋጀነው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይችላሉ።
6. ጨረታው በ8ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ልክ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በሸገር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የሰበታ ከተማ ቅርንጫፍ ይከፈታል። ነገር ግን ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
7. ኤጀንሲው ለጨረታ ማስከበሪያ 1% ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም CPO ከጨረታው ሰነድ ጋር ማስገባት አለባቸው።
8. የስራው አይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
9. ዊዝ ሆልድ ታክስ ለመቁረጥ ፈቃደኛ የሆነ
10. የጨረታ ሣጥን ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
11. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011 338 1383/ 09 42 70 85 56
በሸገር ከተማ የሰበታ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት