Your cart is currently empty!
የመኖሪያ ቤት ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
Addis Zemen(Feb 03, 2026)
2ኛ የጨረታ ማስታወቂያ
በፍርድ ባለመብት አዜብ ነጋሽ እና በፍርድ ባለዕዳ
1 ብዛየሁ እሸቴ
2ኛ ቃላአብ ሲሳይ
3ኛ አፈወርቅ ሲሳይ መካከል ባለው የአፈጻጸም ከርከር አስመልከቶ የዳቤ ከፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በካርታ ቁጥር OR001144409004 በሆነ ስፋቱ 191.27 ካሬ ሜትር ላይ በሐንጋቱ ወረዳ ውስጥ የሚገኘው የመኖሪያ ቤት 1ኛ የፍርድ ባለዕዳ ባለቤት፤ የ2ኛ እና 3ኛ የፍርድ ባለዕዳዎች አባት ሲሳይ ሁንዴ ፈይሣ በሚባል ሰው ስም ተመዝግቦ የሚገኘው ንብረት በመነሻ ጨረታ በ3,779,235 60 (ሶስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰባ ዘጠኝ ሺህ ሁለት መቶ ሃያ አምስት ከ60 ሣንቲም) የተወሰነውን ውሳኔ ለማስፈጸም ጨረታ እንዲወጣ ተደርጓል።
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ለአንድ ወር ጊዜ እስከ ቀን 26/06/2018 ዓ.ም ድረስ በአየር ላይ ስለሚቆይ ቤቱን መግዛት የምትፈልጉ ሰዎች ጨረታው በቀን 26/06/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 እስከ 6፡30 ድረስ የሚካሄድ ስለሆነ ከጨረታው መሻ ዋጋ ግምት ውስጥ 1/4ኛውን /25%/ አስቀድሞ በሲፒኦ (CPO) በባንክ ማስያዝ የሚችሉ መሆኑን፣
- ለሽያጭ የቀረበው ንብረት እስኳሁን በሌላ ዕዳ ወይም በዋስትና መያዙን ቀርቦ የተቃወመ የለም።
- ያሸነፈው ሰው በተባለበት ቀን ውስጥ ከፍሎ ያላጠናቀቀ ከሆነ የቀድሞ ጨረታ ውድቅ ሆኖ አዲስ ጨረታ ይካሄዳል።
- ጨረታውን ያሸነፈው ሰው ሁሉንም ክፍያ ባለመከፈሉ የንብረቱ ሽያጭ ዋጋ የሚወርድ ከሆነ ጨረታውን ያሸነፈው ሰው የተፈጠረውን ልዩነት ለመሸፈን ግዴታ አለበት።
- ማንኛውን ተወዳድሮ ጨረታውን ያሸነፈው ሰው ከላይ የተቀመጠውን መስፈርት እና ያለውን ግዴታ የሚቀበል መሆኑን መስማማት አለበት።
- ጨረታ የሚካሄደው በጨረታ ኮሚቴ ግልጽ በሆነ ጨረታ ተወዳዳሪዎች ወይም የባለጉዳዮቹ ሕጋዊ ወኪል በተገኙበት የሚካሄድ ይሆናል።
ለተጨማሪ መረጃ ቁጥር 09-10-96-98-56
የዳቤ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት