በአብክመ የሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የተለያዩ የተሽከርካሪ መኪኖች የጂፒኤስ እና የእስፔር መለዋወጫ ግዥ በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል


Be’kur(Feb 02, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ የሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት ግዥ

  • የተለያዩ የተሽከርካሪ መኪኖች የጂፒኤስ እና
  •  የእስፔር መለዋወጫ ግዥ

በመደበኛ በጀት ለቢሮው መኪና አገልግሎት የሚውሉ በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በሎት መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ) ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆንናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ ዋጋ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 200 ብር ከግ/ፋይ/ንብ/አስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 213 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የእቃው ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይንም በባንክ የተረጋገጠ ሌተርኦፍ ክሬዲት ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በባህል ቱሪዝም ቢሮ በግ/ፋይ/ንብ/አስ ደጋፊ የስራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 213 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 15ኛው ቀን ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋይ/ንብ/አስ ደጋፊ የስራ ሂደት ክፍል በቢሮ ቁጥር 213 በ16ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ በዛው ቀን በ8፡30 ይከፈታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 213 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 220 42 70 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 58 64 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

በአብክመ የሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *