የመኖሪያ ቤት የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ


Be’kur(Feb 02, 2026)

የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

አፈ/ከሳሽ ሸገር እቁብ ማህበር እና በአፈ/ተከሳሽ እነ ጌትነት መንግት መካከል ባለዉ የገንዘብ ክርክር ጉዳይ በእንጅባራ ከተማ 04 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ መቅደስ ሸፈራው፣ በምዕራብ አለማየሁ አበበ፣ በሰሜን ገብሬ ሙላት እንዲሁም በደቡብ መንገድ መካከል የሚያዋስነውን በአፈ/ተከሳሽ በአቶ ሽፈራው የኔሰው ስም ተመዝግቦ የሚገኝ የመኖሪያ ቤት መነሻ ዋጋን ሳይጠብቅ ስለሚሸጥ የጨረታ ማስታወቂያ ለ30 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ቆይቶ ከየካቲት 02/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መጋቢት 02/2018 ዓ.ም ድረስ በተከታታይ 30 ቀናት በማዋል መጋቢት 03/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6:00 እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ወደ ጨረታው ስትመጡ የጨታውን መነሻ ዋጋ 1/4 ኛውን ሲፒኦ ይዛችሁ እንዲቀርቡ እናሳስባለን፡፡

የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *