የወልዲያ ከተማ አስ/ር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ የድልድይ ዲዛይንና የማማከር ስራ ማሰራት ይፈልጋል


Be’kur(Feb 02, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የወልዲያ ከተማ አስ/ር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በመደበኛ በጀት በ2018 በጀት አመት የሁለት ድልድይ ዲዛይን ስራ /short list/ በማድረግ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

የስራዉ አላማ ለተጠቀሰዉ ስራ የድልድይ ዲዛይንና የማማከር ስራ ለሁለቱም ድልደይ ዲዛይን ስራ መስራት ይሆናል፡፡ ዝርዝር ስራዎች በቢጋር (TOR) ላይ በመወዳደሪያ ሃሳብ ማቅረቢያ (Request for Proposal) ሰነድ ዉስጥ ተዘርዝሮ ቅድመ መረጣውን ለሚያልፍ ተወዳዳሪዎች (short list firms) ይሰጣል፡፡ በመሆኑም ከላይ በተጠቀሰው ስራ ላይ ለመወዳድር ፍላጎትና በቂ ልምድ ያላቸው ቅደመ መረጣ ለማድረግ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. ዘርፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡትን እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. ከዚህ በፊት በዲዛይን ስራና ማማከር ስራ በቂ ል ምድ ያለው ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ለማማክር ስራ ሊያሰማራቸው የሚችሉ ቁልፍ ባለሙያዎች ያሉት እና የትምህርት ዝግጅትና የስራ
  4. ልምዳቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ፡፡
  5. ሌሎች ለቅድመ መረጣ ወይም ውድድር ላይ ያግዛሉ የሚባሉ የድርጅቱን የመፈፀም የአቅም ደረጃና መስሪያ ቁሳቁስ የሚያቀርቡ፡፡
  6. ስራውን ለመስራት ፍላጎት ያለው አማካሪ ድርጅት ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎችን በየ ገጹ የድርጅቱ ማህተምና ሙሉ አድራሻ በመግለፅ ከማመልከቻ ጋር ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያልተደረገበትና ማመልከቻ የሌለው የፍላጎት መግለጫ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ የፍላጎት መግለጫ (Expression of Interest) ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ከየካቲት 25/2018 ዓ.ም እስከ የካቲት 10/2018 ባሉት ተከታታይ ቀናቶች በወልድያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግዥና/ፋ/ ንብ/ አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 13 ተገኝተው ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታውም የቅድመ መረጣ ስራ ፍላጎት የመጨረሻ ቀን የካቲት 10/2018 4፡00 ቅድመ መረጣ ማድረግ ይጀምራል፡፡ ቅድመ መረጣው እንደተጠናቀቀ ላለፉትና ለተመረጡት (short list firms) የመወዳደሪያ ሀሳብ መጠየቂያ ሰነድ ይሰጣቸዋል፡፡ የፍላጎት መግለጫ ሰነዱ በድርጅቱ ህጋዊ ማህተም የተረጋገጠ መሆን አለበት ስርዝ ድልዝ ወይም አሻሚ የሆነ ፅሁፍ መኖር የለበትም መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ የፍላጎት መግለጫ ማስታወቂያውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡ ለተጨማሪ ማብራሪያ ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ስዓት መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ለበለጠ በስልክ ቁጥር 033 331 03 22 /033 331 18 61/ 033 333 1133 መደወል ይችላሉ፡፡

የወልድያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *