የአብክመ ገንዘብ ቢሮ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Be’kur(Feb 02, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር ግጨ 02/2018

የአብክመ ገንዘብ ቢሮ የተለያዩ ሎት1. የፅህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት2. የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት3. የብስክሌት ጎማ፣ ሎት4. የተለያዩ ቦርሳዎች እንዲሁም ሎት4. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን  በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡

1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርቲፊኬት የሚያቀርቡ እንዲሁም የግዥ መጠን ብር ከ200,000 (ከሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀቶችን ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. የጨረታ  ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀናት ገንዘብ ቢሮ ከሚገኝበት ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 03 ከዲፓ መስመር ዝቅ ብሎ ቢሮ ቁጥር 101 ወይም 102 በአካል በመቅረብ የማይመለስ የኢትዩጵያ ብር 250 (ሁለት መቶ አምሳ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻል ሲሆን፤ ሰነዱን ከገዙ በኋላ  የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በመስሪያ ቤቱ  ለዚህ ጉዳይ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የገዙትን የጨረታ ሰነድና አስፈላጊ ሰነዶችን በፓስታዎች በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

3.  ማስታወቂያው በበጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ  ይቆይና በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ፤ በዚሁ ዕለት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባህር ዳር ከተማ በሚገኝው የአብክመ ገንዘብ ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ላይ ይከፈታል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋበት 16ኛው ቀን በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡

4. ተጫራቾች ለሎት1. የፅህፈት መሳሪያ ዕቃዎች ብር 1,600.00፣ ለሎት2. የፅዳት ዕቃዎች ብር 20,000.00፣ ለሎት3. የቋሚነት ባህሪ ያላቸው ዕቃዎች (የተለያዩ ቦርሳዎች) ብር 3,000.00፣ ለሎት 4. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ብር 200,000.00 እንዲሁም ለሎት3.  የብስክሌት ጎማ ከነከለመዳሪው ብር 1,000.00  የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በጨረታው ፓስታ ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡

5. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ/አገልግሎት አይነት ቢሮው ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

6. ጨረታው የሚዘጋጅበት ቋንቋ በአማርኛ ይሆናል፡፡

7. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

8. የሚገዙ እቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ሙሉ ስፔስፊኬሽን)፤መመሪያዎችና የውል ቃሎችን እንዲሁም የዋጋ መሙያ ቅጾችን  ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅተው የቀረቡ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

9. ለበለጠ መረጃ አብክመ ገንዘብ ቢሮ ቢሮ ቁጥር 108 በአካል በመገኝት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 13 56/058 220 08 39 በመደወል ማብራሪያ ማግኝት ይቻላል፡፡

የአብክመ ገንዘብ ቢሮ