በምዕ/ጉጃም ዞን ለደምበጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚሰጡ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Be’kur(Feb 02, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በምዕ/ጉጃም ዞን ለደምበጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚሰጡ እቃዎችን

  • ሎት1. የጽዳት እቃዋች፣
  • ሎት2. የጽህፈት መሳሪያዎች፣
  • ሎት3. የተለያዩ የህክምና ህትመቶች እና
  •  ሎት4. 250kva ጀነሬተር ዓመታዊ ሙሉ ሰርቪስ እና አስፈላጊ ከሆነ መለዋወጫ እቃዎችን ማቅረብ የሚችሉ፤
  •  እንዲሁም ለመለዋወጫ እቃዎችና ለሙሉ ሰርቪስ ለአንድ አመት ዋስትና የሚሰጥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

 ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላችሁና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ወይም ቲን ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ግዥዉ ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ )ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ነፃ ከሆኑ አቅርቦቶች ወይም እንዳይሰበሰብባቸው በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) አዋጁ የተፈቀደላቸው ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፍ ማንኛውም ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ወይም የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸዉ፡፡
  4. የቫት ተመዝጋቢነት የሚጠይቀው በእያንዳንዱ ምድብ ወይም ሎት የሚገዛው የእቃውን ዋጋ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ) እና በላይ ሲሆን ነው።
  5. በስማቸው ስልጣን ከተሰጠው መ/ቤት የታተመ ህጋዊ ደረሰኝ ያላቸው ቢሆን ይመረጣል፡፡
  6. ተጫራቾች ጨረታውን ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማህትም ትክክለኛነቱን በፊርማ በማረጋገጥ ከማጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  7. የሚገዙት እቃዎች ዝርዝር መገለጫ (እስፔሲፊኬሽን ) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8.  የጨረታ ማስከበሪያ ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ላይ አንድ በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሲፒኦ(ሲፒዩ) ወይም በመ/ሂ1 ለደምበጫ የመጀ/ደ/ሆስፒታል በደረሰኝ በመክፈል ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  9.  የግዥ መጠኑ ከፍተኛ ሆኖ የቫት ተመዝጋቢዎች በሚወዳደሩበት ጊዜ የሚያስይዙት የጨረታ ማስከበሪያ አጠቃለይ የተወዳደሩበትን ዋጋ ማለትም ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
  10. የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ሽህ) ብር በመክፈል መግዛት አለበት፡፡
  11. ማንኛዉም ተጫራች በገዛዉ የእቃዎች የዋጋ መሙያ ላይ እስፔስፊኬሽን መጨመርም ሆነ መቀነስ ሳይኖርበት የጨረታ ሰነዱን ገልፆ በመፃፍ ዋጋዉን መሙላት ንግድ ፍቃድ፣ ቲን፣ የጨረታ ማስከበሪያና ሌሎች ማስረጃዎች በአንድ ፖስታ በማድረግ በፖስታዉ ላይ ስም፣ አድራሻ ፊርማና ማህተም በማድረግ ደም/መጀ/ደ/ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 106 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  12. የጨረታው ማስታወቂያ ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚታሰብ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በዚሁ እለት በ15ኛዉ ቀን ከ11፡30 በኋላ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጐ በ16ኛው ቀን 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችዉ በተገኙበት ይከፈታል።
  13. በተራ ቁጥር 12 የተጠቀሰዉ እንደ ተጠበቀ ሆኖ ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  14. መስሪያ ቤቱ የጨረታዉን አሸናፊ የሚለየዉ በሎት ሲሆን እያንዳንዱ የዕቃ ዝርዝር ግን ሙሉ በሙሉ መሞላት አለበት፡፡
  15. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፉባቸውን እቃዎች ያሸነፉበትን ዋጋ ላይ 10በመቶ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  16. አሸናፊዉ ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ደምበጫ የመጀ/ደ/ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 106 ቀርቦ ዉል መፈጸም አለበት፡፡
  17. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  18. የግዥ አቅርቦቱን አሸናፊዉ ዉል በያዘ በ10 ቀናት ዉስጥ እቃዉን በራሱ ትራንስፖርት በማጓጓዝ ደምበጫ የመጀ/ደ/ ሆስፒታል ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡ የጨረታ አሸናፊው ያሸነፈባቸውን እቃዎች በውሉ መሠረት ካላቀረበ በውሉ በተመለከተ የገንዘብ መጠን ላይ በየቀኑ ዜሮ ነጥብ አንድ በመቶ ወይም አንድ ሺህኛ መቀጫ ይከፍላል።
  19. በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 106 ድረስ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 09 70 87 58 44 /09 18 06 21 97 መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ ማንኛውም ተጫራች የመጨረሻ ቀን 11፡30 በኋላ ቢመጣ የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የደምበጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል