Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት የፅዳት እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እና ስቴሽነሪ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 04, 2026)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ 01/18
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት የፅዳት እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እና የስቴሽነሪ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ ስምትፈልጉ ተጫራቾች በሙሉ
1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፤ የንግድ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ፤ የምዝገባ ሰርትፊኬት፤ የመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር አቅራቢዎች ምዝገባ፣ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር፤ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርትፊኬት፣ በዘመኑ የታደሰ ግብር የከፈሉበት ማስረጃ (ታክስ ክሊራንስ) ማያያዝ ይኖርበታል፡፡
2. ለሚወዳደሩባቸው የአገልግሎት አይነቶች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሁሉም ሎቶች ከታች በሠንጠረዡ ላይ የተጠቀሰውን በሲፒኦ ወይም በባንክ የተረጋገጠ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በኢ/ያ በንግድ ባንክ ቁጥር 1000670020308 የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የሚያስችል ለእያንዳንዱ ሎት ብር 300 /ሶሰት መቶ ብር/ በማስገባት በተቋሙ መስሪያ ቤት ፒያሳ ዋስትና የንግድ ማዕከል 16ኛ ፎቅ ከግዥ ከፍል የጨረታ ሰነድ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
4. የጨረታ ሰነድ አቀራረቡ አንድ ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናል አንድ ቴክኒካል ሰነድ ቅጂ፣ አንድ የፋይናንሻል ሰነድ ኦሪጅናል አንድ የፋይናንሻል ሰነድ ቅጂ፣ እንዲሁም ሲፒኦ ለብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ መሆን አለበት፡፡
5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ መግለጽ የሚችሉት የጨረታውን ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከአስፈላጊው ማስረጃ ጋር በማያያዝ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጨምሮ በሠንጠረዥ እስከ ተቀመጠው የመዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ ብቻ ነው፡፡
6 ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድቦንድ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ በማያያዝ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
|
ተ.ቁ
|
የግዥው አይነት
|
ሎት
|
የጨረታ ማስከበሪያ |
የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን |
የጨረታ መዝጊያ ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ሰዓት |
|
1 |
የፅዳት እቃዎች |
ሎት-1 |
20,000.00 |
የካቲት 13 2018 |
ጠዋት 4:00 ሰዓት |
ጠዋት 4:30 |
|
2 |
ስቴሽነሪ እቃዎች |
ሎት-2 |
20,000.00 |
የካቲት 13 2018 |
ጠዋት 4:00 ሰዓት |
ጠዋት 4:30 |
|
3 |
የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች |
ሎት-3 |
30,000.00 |
የካቲት 13 2018 |
ጠዋት 4:00 ሰዓት |
ጠዋት 4:30 |
7. ተጫራቾች ከሎት-1 እስከ ሎት 3 ያሉት ዕቃዎች የተጠቀሱት ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ግዴታ ነው።
8. ጨረታው ከላይ በተጠቀሱት ቀንና ሰዓት በግዥ ከፍሉ – 16ኛ ፎቅ ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰነዱ ይከፈታል።
9. ተቋሙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት