በአብክመ የከሚሴ ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በጽ/ቤቱ ሥር ለሚገኙት ለደንብ ማስከበር እና ለጽዳት ሰራተኞች የሚውል የቢሮ የጽዳት እቃዎች ግዥ ለመፈፀም በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 04, 2026)

የቢሮ የጽዳት እቃዎች ግዥ የግልጽ
ጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ የከሚሴ ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በጽ/ቤቱ ሥር ለሚገኙት ለደንብ ማስከበር እና ለጽዳት ሰራተኞች የሚውል የቢሮ የጽዳት እቃዎች ግዥ ለመፈፀም በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ፍቃደኛ የሆነ ፤

1. የቢሮ የጽዳት እቃዎች ግዥ ህጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና ያሳደሱ፤ ለስራው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/TIN/ ያላቸው ፤

2 የጨረታው ሰነድ ከከሚሴ ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 33 በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ ዋና የስራ ሂደት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ 21/ለሀያ አንድ ተከታታይ ቀናት ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዋናና ኮፒ በመያዝ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ለእያንዳዱ ሰነድ የማይመለስ የኢትዮ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

 3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ኮፒ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፖች በአብክመ የከሚሴ ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የስራ ሂደት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሀያ ሁለተኛው/22/ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ የቢሮ የጽዳት እቃዎች ግዥ ጨረታ ሰነድ ባለው ጊዜ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4. ጨረታው 18/6/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 የቢሮ የጽዳት እቃዎች ግዥ ላይ በግዢ ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

5. ተጫራቾች ተመላሽ የሚደረግ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ የቢሮ ቋሚ እና አላቂ እቃዎች ግዥ ከጠቅላላው ድምር 8,000 (ስምንት ሺህ ብር በጥሬ ገንዘብ ወይንም በባንክ ትእዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው።

6. ለቢሮ የጽዳት እቃዎች ግዥ የጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚዋዋልበት ጊዜ የውለታ ማስከበሪያ ከአጠቃላይ ድምር ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል።

7 መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8. ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ፤ በከሚሴ ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በግንባር በመቅረብ ወይንም በስልክ ቁጥር 033 554 0255 ደውለው መረዳት ይችላሉ።

በአብክመ የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማ
እና መሰረተ ልማት ጽ / ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *