የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል


Reporter(Feb 04, 2026)

የሐራጅ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል።

.

የተበዳሪው ስም

የንብረት አስያዥ ስም

የመያዣ ንብረቱ መለያ

የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ብር)

ሐራጁ የሚከናወንበት ቀን እና ሰዓት

አድራሻ

የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር

የይዞታው ስፋት (.)

የይዞታው አይነት/ የሚሰጠው አገልግሎት

1

በርሆት የምግብ ማምረቻ /የተ/የግ/ማህበር

አቶ ሲራክ ብርሃኑ ፈይሳ

በአዲስ አበባ /የካ/// ወረዳ 12

LMK1281 433401226614222

1,226.61

ቅይጥ

67,644,194.54

30/06/2018 . 300-400 ጠዋት

2

አቶ ተመስገን ጫላ ጃለታ

ተበዳሪው

በሸገር ከተማ ፉሪ// የቀድሞ ወረዳ 4

L/349/2003/B6/P1

468

የመኖሪያ ቤት

21,582,351.71

30/06/2018 . 400-500 ጠዋት

3

አቶ ያሬድ ገሮ /ሚካኤል

ተበዳሪው

ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ከፋ ዞን ቦንጋ ወረዳ ቦንጋ ከተማ 02 ቀበሌ

311/ገገ-66/2012

300

የመኖሪያ ቤት

11,639,876.63

30/06/2018 . 500-600 ጠዋት

4

አቶ ለገሰ ሙለታ ያሚ እና የሰውዘር አለበል ኃይሉ

ተበዳሪው

ሻሸመኔ ከተማ አለቼ /ከተማ አዋሾ ወረዳ 01 ቀበሌ

WBIFBG/A/L/937/09

5000

ለፋብሪካ አገልግሎት የሚውል ሕንጻ

38,071,965.73

30/06/2018 . 300-400 ጠዋት

በመሆኑም፡

1. ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4 በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላል:: የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲፒኦ ማቅረብ ተመራጭ ነው።

2. ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱት ንብረቶቹ ጨረታ የሚከናወነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋናው መስሪያ ቤት 42 (ወለል) ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4203 ሲሆን፤ በተራ ቁጥር 4 ላይ የተጠቀሰው ንብረት ጨረታ የሚከናወነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻሸመኔ ዲስትሪክት ቅጥር ጊቢ ነው።

3. የንግድ ማህበርን ወክሎ ለመጫረት የማህበሩን መመስረቻ እና መተዳደርያ ደንብ የያዘና በማህበሩ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል።

4. ከመኖሪያ ቤቶች በስተቀር ለጨረታ የቀረቡ ንብረቶችን በጨረታ አሸንፎ የገዛ በሽያጩ ገንዘብ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል።

5. የጨረታ አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል።

6. ንብረቶቹን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት 42 ፎቅ በአካል በመቅረብ ባንኩ በሚያመቻቸው ፕሮግራም መሰረት መጎብኘት ይቻላል።

7. በጨረታው ከፍተኛ የሆነ የጨረታ ዋጋ የሰጠ ተጫራች በባንኩ የጨረታ አሸናፊነት ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ቀሪ የሽያጩን ገንዘብ 15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ለሐራጁ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።

8. ንብረቶቹን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ 15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም:: ገዢው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን የወስዳል።

9. ባንኩ ሐራጁን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111-13-05-08 በመደወል ወይም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋና /ቤት 42 ፎቅ ወይም ሻሸመኔ ዲስትሪክት በስልክ ወይም በአካል ቀርቦ ማነጋገር ይቻላል።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *