Your cart is currently empty!
በጉለሌ ክ/ከ/ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ፅህፈት መሳሪያ፣ መኪና እቃ፣ የደንብ ልብስ፣ ዘር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 04, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 004/2018 ዓ/ም
በጉለሌ ክ/ከ/ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ መደበኛ ለ2018 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1፡- ፅህፈት መሳሪያ
- ሎት 2፡- መኪና እቃ
- ሎት 3፡- የደንብ ልብስ
- ሎት 4፡- ዘር
- ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን፣ አድራሻቸውንና ፊርማቸውን በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ማስፈር ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ጨረታ ፖስታ ላይ ለየትኛው እቃ ወይም አገልግሎት እንደሚወዳደሩ በግልጽ ለይተው መጻፍ አለባቸው።
- ተጫራቾች በመንግስት ግዢ ኤጀንሲ ድረ ገጽ (ዌብ ሳይት) ላይ በዘርፉ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ እንዳላቸው የሚያረጋግጥ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች ላይ ወይም አገልግሎቶች ሳምፕል ወይም ናሙና ለመስራቤቱ በማቅረብ የጥራትና የቴክኒክ ኮሚቴዎች ደረጃቸውን የጠበቁ ስለመሆናቸው ይገመገማሉ።
- ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ የተዘረዘሩት እቃዎች ላይ የቀረበውን እስፔሲፊኬሽን በመሰረዝ በመደለዝ ማሻሻያ ማድረግና መለወጥ አይችሉም።
- በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጃችሁ ተጫራቾች ካደራጃችሁ አካል የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫት ያካተተ መሆኑን ወይም ዋጋው ከቫት ውጪ መሆኑን በግልጽ ማስቀመጥ አለባቸው።ይህ ባይሆን ዋጋው ቫት ያካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላው ዋጋ ለሎት 1፡- 10,000 ፤ ለሎት 2፡- 10,000፤ ለሎት 3፡- 10,000፣ለሎት 4፡10,000 እና የጠቅላላ ዋጋ ሲፒኦ ከጨረታው ሰነድ ጋር አብረው ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዶች በሙሉ በኢንቨሎፕ ታሽገው ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት ለየብቻው በማድረግና በማያያዝ ፊርማቸውንና ማህተማቸውን በፖስታዎች ላይ በማኖር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሰነድ በመክፈል በስራ ሰዓት ጉለሌ ክፍለ ከተማ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 15 የጉ/ክ/ከ/አ/ የዲዛይን ና ግንባታ ስራዎች ፑል/የአስ/ፋይ/ፅ/ቤት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- የካፒታል መጠናቸው ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በላይ የሆነ ተጫራቾች ከሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ጊዜ የሚያበቃው የስራ ቀን ከሆነ በ10 ተከታታይ ቀናቶች በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆንን እየገለጽን ጨረታው አየር ላይ በዋለ 11ኛው ቀን ባለው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 4፡30 በጉ/ክ/ከ/የዲ/ግ/ስ/ፑል/የአስ/ፋይ/ፅ/ቤት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።
- ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው የሚሰረዙ ይሆናሉ።
- ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
- ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት ጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል ይህ ባይሆን ከጨረታ ይሰረዛሉ።
- ተጫራቾች በንግድ ፈቃዳቸው በስተጀርባ ላይ የተዘረዘሩትን የንግድ ዘርፍ አይነቶች ኮፒ አድርገው ማቅረብ አለባቸው። የተጫራቾች ማህተም እና የንግድ ፍቃዳቸው እንዲሁም የደረሰኛቸው ስያሜ አንድ አይነት መሆን ይኖርበታል።
- በጨረታ መወዳደሪያ የሚያቀርብ ዋጋ ለስድስት ወር ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል።
- ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች ከመ/ቤታችን ጋር ውል ማስከበሪያ ላሸነፉባቸው ዕቃዎች የጠቅላላ ዋጋውን 10% ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል ይህ ባይሆን ግን በጨረታ ያስያዙት /ሲፒኦ/ በቀጥታ ለመንግስት ገቢ ሆኖ ከጨረታው ይሰረዛሉ።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ እንዲሁም በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን የእቃ ብዛት ቀንሶ ወይም ጨምሮ ከአሸነፈው ድርጅት የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ የተዘረዘሩት እቃዎች ላይ የቀረበውን እስፔሲፊኬሽን በመሰረት ናሙና ወይም ሳምፕል ማስገባት ይኖርበታል።
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን የእቃ ብዛት 20% ቀንሶ ወይም 20% ጨምሮ ከአሸነፈው ድርጅት የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሣሰቢያ
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈስገም
በስልክ ቁጥር 011-812 1096
ጉለሌ ክ/ከ/ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት
cttx Agriculture and Farming cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Products and Services cttx, cttx Raw Materials and Supplies cttx, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Spare Parts and Car Decoration Materials cttx, cttx Stationery cttx, cttx Textile, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx