Your cart is currently empty!
አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ./ የመኖሪያ ቤት ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Reporter(Feb 04, 2026)
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ /አማ/ የሰጠው ብድር ባለመከፈሉ የብድር መያዣ ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ሙሉ ስም |
የመያዣ ስጪው ስም |
ከተበዳሪው የሚፈለግበት ቀሪ ዕዳ |
የንብረቱ ዓይነትና አገልግሎት |
የቦታው ስፋት
|
የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ
|
የጨረታ መነሻ ዋጋ በብር |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀን
|
የምዝገባ ሰዓት
|
የጨረታ ሰዓት
|
ጨረታው የወጣበት ጊዜ
|
|
1 |
አቶ መላኩ ደማሙ ካሳ |
ተበዳሪው
|
እስከ ጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም ብር 1,775,561.29 |
መኖሪያ ቤት
|
450 ካ.ሜ
|
1060/6/17/2
|
በቤጉክ/መ ግልገል በለስ ከተማ 01 ቀበሌ |
1,274,400.00 |
የካቲት 27 ቀን 2018 ዓ.ም
|
4:00-5:30
|
5:30_ 6:00
|
ለሁለተኛ ጊዜ
|
|
2 |
አቶ አዕምሮ ሙሉዬ ምህረቴ |
ሙሉነሽ አድማስ ተገኜ |
እስከ ጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም ብር 4,664,598.65
|
መኖሪያ |
70.75ካ.ሜ
|
የይዞታ ልዩ መለያ ቁጥር AA000070401639/201160003 የቤት ቁጥር B-116/03 |
አዲስ አበባ፣አቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 04
|
4,169,339.49
|
የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም
|
4:00-5:30
|
5:30_ 6:00
|
ለመጀመሪያ ጊዜ
|
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት/ንብረቶች መረከብ ይኖርበታል:: በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል:: በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
- ተበዳሪው/መያዣ ሰጪው በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎችንም ገዢ ይከፍላል። ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ቀሪ የሊዝ ክፍያ ገዢ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል።
- ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አሲዞ ለመጎብኘት ወይም ለማየት ይቻላል።
- በባንኩ ብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟሉ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢዎች ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
- የጨረታው ቦታ ንብረቶቹ በሚገኙበት ስፍራ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 058-320-96-60 ባህር ዳር በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።