በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት በካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ፋ/ኢል/ጽ/ቤት አነስተኛ መስኖ ግንባታ ሥራ ከሕጋዊ ሥራ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 04, 2026)

የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዢ መ/ቁ ESWEPR-526662 CW-REQ በዲታ ወረዳ የሺሚ አነስተኛ መስኖ ልማት ፕሮጀክት የፕሮጀክቱ ስም ምግብ ሥርዓት ማጠናከርያ /FSRP/

1/ በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት በካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ፋ/ኢል/ጽ/ቤት ለወረዳ ግብርና አ/ጥ/ ሕ/ስ/ ጽ/ቤት በምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም በጀት ድጋፍ በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት በወረዳው ሙቲ ቀበሌ የሸሚ አነስተኛ መስኖ ግንባታ ሥራ ከሕጋዊ ሥራ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።

2/ በዚህም መሠረት ለ2018 ዓ/ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ም/ወረቀት፣ የተ/እ/ታ(ቫት) ምዝገባ ም/ወረቀት፣ የግብር ከፋይመለያ(TIN) ም/ወረቀት GC/WC ደረጃ 5 እና ከዛ በላይ ብቃት ማረጋገጫ ያለው፤- የመንግሥትን ግብር ስለመክፈላቸው ከገቢዎች የክሊራንስ ደብዳቤ ያቀረበ እንዲሁም በተጠቀሰው ግንባታ ዘርፍ በአቅራቢነት ስለመመዝገባቸው የም/ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ አቅራቢዎች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

3/ተጨማሪ መረጃዎች በጨረታ ሰነዱ /Bid document/ ላይ የሚገለጽና የሚሞላ ይሆናል።

4/ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 30 ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት ብቻ ለወረዳው ገቢዎች ጽ/ቤት የማይመለስ 500 ብር በፊደል አምስት መቶ ብር ብቻ በመክፈል ከመ/ቤታችን የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ግዢ ቢሮ ቁጥር 06 መውሰድ ይችላሉ።

5/ ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበትን ፋይናንሻል ኦርጅናል ሰነድ በአንድ ፖስታ ፤ኦርጅናል ቴክኒካል መረጃዎችን በአንድ ፖስታ፤ፋይንሻል ዶክመንት ሁለት ኮፒ፤ ቴክኒካል መረጃ ኮፒ በማድረግ በእናት ፖስታ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠሩ ተከታታይ 31ኛ ቀን ዴቻ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀ ሳጥን 10፡00 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በ31ኛ ቀን 10፡00 ታሽጎ በዕለቱ 10፤30 የሚከፈት ስሆን ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።

6/ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 350000 (ሶስት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ማስያዣ (CPO) ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

7/ መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8/ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 047 772 0383/ 09 17 10 15 40/ 09 79 74 87 26 ደውለው መረዳት ይችላሉ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ካፋ ዞን
የዴቻ ወረዳ ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *