Your cart is currently empty!
በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት ካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት አነስተኛ ድልድይ ግንባታ ሥራ ከሕጋዊ ሥራ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 04, 2026)
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ የግዢ መ/ቁ ET-SWEPR-526547 CW-REQ በዲታ ወረዳ የሺሚ አነስተኛ ድልድይ ልማት ፕሮጀክት
የፕሮጀክቱ ስም ምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም/FSRP/
1/ በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት ካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለወረዳ ግብርና አ/ጥ/ ሕ/ስ/ ጽ/ቤት በምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም በጀት ድጋፍ በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት በወረዳው ማልጋዋ ቀበሌ የሺሚ አነስተኛ ድልድይ ግንባታ ሥራ ከሕጋዊ ሥራ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
2/ በዚህም መሠረት ለ2018 ዓም የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ም/ወረቀት፣ የተ እ/ታ(ቫት) ምዝገባ ም/ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ(TIN) ም/ወረቀት፣ GC/BC/RC ደረጃ 5 እና ከዛ በላይ ብቃት ማረጋገጫ ያለው፤- የመንግሥትን ግብር ስለመክፈላቸው ከገቢዎች የከሊራንስ ደብዳቤ ያቀረበ እንዲሁም በተጠቀሰው ግንባታ ዘርፍ በአቅራቢነት ስለመመዝገባቸው የም/ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ አቅራቢዎች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
3/ ተጨማሪ መረጃዎች በጨረታ ሰነዱ /Bid document/ላይ የሚገለጽና የሚሞላ ይሆናል።
4/ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 30 ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት ብቻ ለወረዳው ገቢዎች ጽ/ቤት የማይመለስ 500 ብር በፊደል አምስት መቶ ብር ብቻ በመክፈል ከመ/ቤታችን የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ግዢ ቢሮ ቁጥር 06 መውሰድ ይችላሉ።
5/ ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበትን ፋይናንሻል ኦርጅናል ዶክመንት በአንድ ፖስታ ቴክኒካል ኦርጅናል መረጃዎችን በአንድ ፖስታ ፤ ፋይናሻል ዶክመንት ሁለት ኮፒ ቴክኒካል መረጃ ሁለት ኮፒ በማድረግ በእናት ፖስታ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠሩ ተከታታይ 31ኛ ቀን ዴቻ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀ ሳጥን 8፡00 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በ31ኛ ቀን 8፡00 ታሽጎ በዕለቱ 8፡30 የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
6/ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 350000(ሦስት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ማስያዣ (CPO) ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
7/ መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
8/ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 047 772 0383/ 09 17 10 15 40/09 79 74 87 26/ ደውለው መረዳት ይችላሉ።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ካፋ ዞን
የዴቻ ወረዳ ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት