የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ሰርቨር ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተርና ፕሮጀክተር እና የተለያዩ አይነት ኤሌክትሮኒክስ አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 05, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 11/2018

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ ለትምህርት ቤቶች አገልግሎት የሚውል በመደበኛ እና በኢቶል በጀት ግዥ ለማከናወን ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ፦

  • ት አንድ – ሰርቨር ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተርና ፕሮጀክተር ( በመደበኛ በጀት )
  • ት ሁለት – የተለያዩ አይነት ኤሌክትሮኒክስ ( በኢቶል በጀት)

ከዚህ በላይ ለተዘረዘሩት በውድድር መስፈረት መሰረት ለመሣተፍ የሚፈልጉ ፡

  1. በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥርና ያላቸው መሆን አለባቸው፤ የተጨራቾች የአቅሪቢነት ምዝገባ
  2. ተጫራቶች ዋጋቸውን የሚገልፀውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ ከግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት አለባቸው፤
  3. የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 – 6፡00 ድረስ ብቻ ለዚህ አላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን 9፡00 ሰዓት ይከፈታል፣ ሆኖም ከ11ኛው ቀን የስራ ቀን በማይሆንበት ጊዜ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀስው ጊዜና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ90 ቀን ጸንቶ የሚቆይ ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻ ብር 50,000.00 / ሃምሳ ሺህ / በሲፒኦ ወይም አንኮንድሻናል ባንከ ጋራንቲ ማቅረብ መወዳደር አለባቸው፤
  6. ተጫራቾች ጨረታውን በሚወዳደሩበት ጊዜ በ2 ፖስታ በማሸግ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክመንት ለየብቻ በማድርግ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስት በቴክኒካል ኦርጅናል ውስጥ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፤
  7. ጨረታው ለ3 ወራት /90 ቀናት ብቻ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል።
  8. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል ከግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ግዥ ክፍል ቁጥር 14 ማግኘት ይቻላል፡
  9. ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡- ሽያጩ ቫትን ጨምሮ ከብር 20.000.00 /ሀያ ሺህ ብር/ በላይ ለሆነው ግዥ 50% ቫት ቀንሰን የምናስቀር መሆኑን እንገልፃለን።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 046212-4302/03

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *