በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ቤት የደንብ ልብስ እና የጽዳት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 05, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 003/522/2018 ዓ.ም

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳው አገልግሎት የሚውል ማለትም

  • ሎት አንድ (1) የደንብ ልብስ፣ እና
  • ሎት ሁለት (2) የጽዳት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

  1. የዘመኑን በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
  5. በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃ ከ(egp/ www.ppa.gov.et ) ፕሪንት አድርገው ማቅረብ የሚችሉ
  6. ናሙና ለተጠየቀባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ የሚችሉ።
  7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃዎች ማለትም ለሎት አንድ (1) የደንብ ልብስ ብር 15,000፤ ለሎት ሁለት (2) የፅዳት እቃዎች ብር 30,000 የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዥያ ትእዛዝ CPO ብቻ (አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር) በሚል አሠርተው ማቅረብ አለባቸው።
  8. እንዲሁም አሸናፊ የሚሆኑ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል። ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
  9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት (10) አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ተዘግቶ በእለቱ ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 017 በመቅረብ የማይመለስ ብር 300 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ
  11. ተጫራቾች የሚያስገቡት ናሙና የቅርብ ጊዜ የፋብሪካ ምርት መሆን ይኖርበታል። ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑበትን እቃ በትከክል ከናሙና ጋር መሳ ለመሳ / ከስፔሲፊኬሽን ጋር መመሳሰል ይኖርበታል።
  12. ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ በኋላ እቃዎቹ ገበያ ላይ ጠፉ፣ ዋጋ ጨመረ የሚል ምክንያት ፍጹም ተቀባይነት የለውም።

ማሳሰቢያ፡- መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ ፡-ቃሊቲ ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ገባ ብሎ

ስልክ ቁጥር፡ 011-471-7931

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *