የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የ5ኛ ዙር የቤቶች ሽያጭ የጨረታ ማራዘሚያ ማስታወቂያ አውጥቷል


Addis Zemen(Feb 06, 2026)

የ5ኛ ዙር የቤቶች ሽያጭ የጨረታ ማራዘሚያ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር ፌቤ.ኮ/ብግጨ/አገ/05/5/2018

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብግጨ/አገ/05/5/2018 የቤቶች ሽያጭ ጨረታ ጥር 09/ 2018 ዓ.ም ታትሞ በወጣው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የጨረታ ማስታወቂያውን ማውጣቱ ይታወቃል።

ሆኖም ከላይ በተገለፀው ቀን ታትሞ በዋለው ጋዜጣ ላይ በጨረታ ማስታወቂያ ተራ ቁጥር 5 ላይ ጨረታው ለ21 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ እንዲውልና ጥር 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 11፡00 ሰአት እንደሚያበቃ የተገለፀ ቢሆንም ከተወዳዳሪዎች በቀረበ የጨረታ ማራዘሚያ ጥያቄ መሰረት ለተጨማሪ 7ቀናት ማለትም ከጥር 29 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ የካቲት 06 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ መሆኑን እያሳወቅን፤ የጨረታ ማራዘሚያ ማስታወቂያው የጨረታ ሰነዱ አካል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ

በስልክ ቁጥር 09-22-49-18-85/09-10-18-59-48 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ዌብሳይት/Website WWW.fhc.gov.et

የፖ.ሣ.ቁ.P.0. Box 299

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን

ከዚህ በፊት የወጣውን ጨረታ ለመመልከት እባክዎን ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ 

https://tender.2merkato.com/tenders/696b5c1a0a538ab0e2000001 


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *